በህወሀት ወንጀለኛ ቡድን ላይ የመጨረሻው የዘመቻው ምዕራፍ መጀመሩን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመቀሌና የአካባቢው ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰቡ። አማራ ሚ…

በህወሀት ወንጀለኛ ቡድን ላይ የመጨረሻው የዘመቻው ምዕራፍ መጀመሩን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመቀሌና የአካባቢው ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰቡ። አማራ ሚ…

በህወሀት ወንጀለኛ ቡድን ላይ የመጨረሻው የዘመቻው ምዕራፍ መጀመሩን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመቀሌና የአካባቢው ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 3013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ለሕወሓት ወንጀለኛ ቡድን የተሰጠው በሰላም እጅ የመስጫ የ72 ሰአት ጊዜ መጠናቀቁን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመቀሌና የአካባቢው ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበዋል። በዚህም ሕግ የማስከበር ዘመቻው የመጨረሻው ምዕራፍ በይፋ መጀመሩን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰጠው የ72 ሰዓታት ጊዜም በሺዎች የሚቆጠሩ የወንጀለኛው ቡድን ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት መስጠታቸውንም አስታውቀዋል። ለመቀሌ እና ለአካባቢው ነዋሪዎች ባስተላለፉት መልዕክትም”የመከላከያ ሠራዊታችን የመጨረሻውንና ሦስተኛውን የዘመቻውን ምእራፍ እንዲፈጽም ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡”ሲል ገልፀዋል። “በዚህ ዘመቻችን ለንጹሐን ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ በሕዝባችን ላብ የተሠራችው የመቀሌ ከተማ የከፋ ጉዳት እንዳያገኛት የሚቻለው ሁሉ ይደረጋል፡፡” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ “ቅርሶች፣ ቤተ እምነቶች፣ የሕዝብ መገልገያዎች፣ የልማት ተቋማትና የሕዝብ መኖሪያዎች የጥቃት ዒላማ እንዳይሆኑም ሁሉም ዓይነት ጥንቃቄ ይደረጋል፡፡”ብለዋል። “የመቀሌና የኣካባቢው ሕዝባችንም ትጥቁን ፈትቶ በቤቱ በመቀመጥና ከወታደራዊ ዒላማዎች በመራቅ፣ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን፡፡” ብለዋል ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በመልዕክታቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply