በህወሃት ውስጥ ያለው ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ ሰውሯቸዋል- የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች

በህወሃት ውስጥ ያለው ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ ሰውሯቸዋል- የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህወሃት ውስጥ ያለው ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ እንደሰወራቸውና እስካሁንም ያሉበት እንደማይታወቅ የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የዳንሻ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ከጽንፈኛው የህወሓት ቡድን ነፃ መውጣቷን አስመልክቶ ደስታቸውን ገልፀዋል።
የከተማዋ ጤና ተቋማት፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ የትራንስፖርትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተከፍተው ነዋሪዎች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ገብተዋል።
ነዋሪዎቹ የህወሃት ፅንፈኛ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የክህደት ጥቃት ከማድረሱ በፊት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ይደርስባቸው እንደነበርም ይናገራሉ።
በሰርግና በለቅሶ ላይ በአለባበሳቸው ጭምር በህወሃት ካድሬዎችና የፀጥታ ኃይሎች ይጠየቁ እንደነበር በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።
ዜጎች መብታቸውን ሲጠይቁ የሚታሰሩበት፣ የሚገረፉበት እንዲሁም የሚገደሉበት ሁኔታ እንደነበርም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ቡድኑ እስካሁን ድረስ ሕዝቡን በቅኝ ግዛት ይዞ በማቆየቱ ለውጥና ሰላም እንዳይመጣ ሲሰራ እንደነበርም ነዋሪዎቹ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በአሁኑ ወቅት መንግሥት በጽንፈኛው የህወሃት ታጣቂ ኃይል ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
በቀጣይ መከላከያ ሰራዊቱን ለማጠናከር ድጋፍ እናደርጋለንም ብለዋል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽንፈኛ ቡድን እስከሚደመሰስ ድረስ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንዲደግፍ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

The post በህወሃት ውስጥ ያለው ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ ሰውሯቸዋል- የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply