በህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ለጥፋት ተልዕኮ ያዘጋጃቸው ከ355 በላይ የተለያየ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

በህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ለጥፋት ተልዕኮ ያዘጋጃቸው ከ355 በላይ የተለያየ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ለጥፋት ተልዕኮ ያዘጋጃቸው የጦር መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደገለጹት፤ መዲናዋን ለማወክ ቡድኑ ያዘጋጀው ከ355 በላይ የተለያየ የጦር መሳሪያ ከ14 ሺህ በላይ ጥይቶች ጋር ተይዘዋል።
የጥፋት አጀንዳውን በማስፈጸም የተጠረጠሩ 162 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የጥፋት ተልዕኮውን ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ ያደረገውን አስተዋጽኦ አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል።

The post በህወሃት ውስጥ ያለ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ለጥፋት ተልዕኮ ያዘጋጃቸው ከ355 በላይ የተለያየ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply