በህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ላይ የተመሰረተው ክስ ተቋረጠ 

በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክሳቸው መቋረጡን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ። የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21፤ 2015 ባወጣው መግለጫ፤ ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነት በተመለከተ “በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ” ከስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚሁ መግለጫው በህወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ የተቋረጠው፤ በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት መሆኑን ጠቁሟል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

[በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይታከሉበታል]

The post በህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ላይ የተመሰረተው ክስ ተቋረጠ  appeared first on Ethiopia Insider.

Source: Link to the Post

Leave a Reply