በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት መካከል አሁንም ተጨባጭ አለመተማመን እንዳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።የፌ…

በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት መካከል አሁንም ተጨባጭ አለመተማመን እንዳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

የፌዴራል መንግስቱ በቅርቡ  የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ አፈፃፀም መገምገሙን አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።

በስብሰባው  በፕሪቶሪያ የተፈረመው ግጭት የማቆም ሥምምነት አተገባበር እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ የስራ አፈፃፀም አጀንዳዎች ትኩረት ማግኘታቸውን አቶ ጌታቸው  ትናንት ማምሻውን ለክልሉ የመገናኛ ብዙሐን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

በፌዴራል መንግስቱ እና የትግራይ ክልል  አመራር መካከል ተጨባጭ አለመተማመን መኖሩን  የገለፁት አቶ ጌታቸው ረዳ “የመጣ ገንዘብ ቢመጣ ትጥቃችሁን ልትፈቱ ፍላጎት የላችሁም፤ ሰራዊታችሁን ልታጠናክሩ ነው የምትሹት» የሚሉ ሀሳብ ከፌደራሉ መንግስት በኩል መቅረቡን በመግለጫቸው አንስተዋል።
ነገር ግን በስብሰባው የተሳተፉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና የህወሓት

አመራሮች “ህልውናችንን ከማረጋገጥ ውጭ፥ ሀገር የመበጥበጥ ፍላጎት” እንደሌላቸው ማስረዳታቸውን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው “ከምንም በላይ በሰላም የመኖር፤ የትግራይ ህዝብን ፍላጎት ከማረጋገጥ ባለፈ አካባቢ የማመስ ይሁን፥ በአንድም በሌላም መንገድ የማእከል ስልጣን የመመኘት ፍላጎት እንደሌለን በደንብ ለማስረዳት ሞክረናል” ሲሉ መናገራቸውን ተዘግቧል።

የህወሓት ሕጋዊ ፓርቲነት የሚረጋገጥበት ሁኔታ እንዲፈጠር ከስምምነት መደረሱንም አቶ ጌታቸው ጠቅሰዋል።
 

የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply