በህዳር ወር ከ268 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ መቻሉ ተገለፀ

በህዳር ወር ከ268 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ መቻሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህዳር ወር ከ268 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ ተችሏል፡፡

ግምታዊ ዋጋቸው ብር 213,620,309 የሆኑ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ-ወጥ ገንዘብ ግምታዊ ዋጋቸው 54,526,384 ብር ወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ-ወጥ ገንዘብ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላይ በህዳር ወር 268,146,693 ብር የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ ተችሏል፡፡

በገቢ ከንትሮባንድ ከተያዙ እቃዎች ከፍተኛውን ደረጃ የያዙት ኤሌክተሮኒክስ፣ ኮንትሮባንድ ጭነውና በኮንትሮባንድ የገቡ ተሽከርካሪዎች፣ አዳዲስ አልባሳት፣ ኮንትሮባንድ ጭነው የተቀጡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ምግብና መጠጥ ነክ ቁሳቁሶች ናቸው፡፡

ገቢ ኮንትሮባንድ በስፋት የተያዘበት ጅግጅጋ፣ ሀዋሳ፣ ድሬደዋ፣ ሞያሌ እና አዋሽ ሲሆኑ ሌሎች ቅረንጫፍ ፅ/ቤቶችም በየደረጃው ገቢ ኮንተሮባንድን መያዝ ችለዋል፡፡

በብዛት የተያዙ ወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች አደንዛዥ እፅ፣ የግብርና ምርቶች፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም ማዕድናት እና የቁም እንስሳት ናቸው፡፡

በወጪ ኮንተሮባንድ ቁጥጥር ሞያሌ፣ አዋሳ፣ ባህርዳር፣ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እና ድሬደዋ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ፤ አሶሳ፣ ጅማ፣ ጅጅጋ እና ጋላፊ በተመሳሳይ የተሻለ የቁጥጥር ስራ ሰርተዋል፡፡

በዚህ ተግባር የተሳተፉ 95 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን ተጠርጣሪዎች በጉምሩክ፣ በክልል ፖሊስ፣ በፌዴራል ፖሊስና በመከላከያ አባላት የተያዙ መሆናቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post በህዳር ወር ከ268 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የገቢና የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ መቻሉ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply