በህገወጥ ዕርድ ምክንያት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ይታጣል ተባለበዓመት በህገወጥ ዕርድ ምክንያት 1.35 ቢሊየን ብር እንደሚያጣ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታውቋል፡፡ድርጅቱ ከ15 ሺህ ኪ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/DO8cC7r1E6odPevDiLcljG7L6DV5tC1MKIA0-Dxbv6srBcx3PeCZVPkyKJ_MBDpfPy5Ex-KEbk0auA9aejCFOlLTMj3EDuzVj0moFuiK8TmQ6ENXkTAOr0ed5yGTVHi8XxrBoKoltnJl-JZ52ecw1sZ2V0JxsTZEdaLrsf2ZxvN0g7nUqIXLThur40U7Wuf28ksR8HYKcG7arI3qkSvKcnsXP0iXIF9Twm3FJupeFDpygkXuAmRuWXPAzC7WBocu2H_HNgB_LoNcCslDTzxKmBf4GRQxJj8kd_jQ96NIZAWi79MH6oJjbt5jYd7ATY1yaSX315JEwEubEmhcELBSpw.jpg

በህገወጥ ዕርድ ምክንያት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ይታጣል ተባለ

በዓመት በህገወጥ ዕርድ ምክንያት 1.35 ቢሊየን ብር እንደሚያጣ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ከ15 ሺህ ኪሎግራም በላይ ህገወጥ ዕርድ ማስወገዱንም ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በ1ሺህ2 መቶ41 የስጋ ሽያጭ ቤቶች ላይ ባደረገው ክትትል 2መቶ41 ቤቶች ሙሉ ለሙሉ እና በከፊል ህገወጥ ስጋ ይዘው የተገኙ መሆናቸውን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እድሪስ ተናግረዋል፡፡

ክትትል በተከናወነባቸው ቤቶች ላይ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 15 ሺህ 2መቶ 94 ኪሎግራም ህገወጥ ዕርድ ማስወገዱን ተገልቷል፡፡

ምርመራ እና ክትትል ከተደረገባቸው 1ሺህ2 መቶ41 ቤቶች ውስጥ 85 ቤቶች የታሸጉ እና ቅጣት እንዲከፍሉ መደረጋቸው ተነግሯል።

እሌኒ ግዛቸው

ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply