በህግ ማስከበሩ ዙሪያ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስረዳት በኩል የተሳካ የዲፕሎማሲ ስራ ተሰርቷል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በህግ ማስከበሩ ዙሪያ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስረዳት በኩል የተሳካ የዲፕሎማሲ ስራ ተሰርቷል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረው ህግ የማስከበር እና የህልውና ዘመቻ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስረዳት በኩል የተሳካ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱን አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደተናገሩት ህግን የማስከበር እርምጃው ዋና ዓላማዎችና ተያያዥ ጉዳዮች በማስረዳት በኩል የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው የልዑካን ቡድን በአፍሪካ እና በአውሮፓ ያደረጋቸው የዲፕሎማሲ ስራዎች የተሳኩ እንደነበሩ ነው የገለጹት አምባሳደሩ፡፡

አምባሳደሩ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በኩልም በተለያዩ ሀገራት በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡

ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን በተመለከተም ወደ ሀገር ውስጥ ለመመለስ የተፈናቃዮች ቁጥር፣ ማንነት፣ የት እንደሚገኙ እና መሰል መረጃዎችን ለማጣራት ከሱዳን ኤምባሲ ጋራ በጋራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በለይኩን አለም

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

The post በህግ ማስከበሩ ዙሪያ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በማስረዳት በኩል የተሳካ የዲፕሎማሲ ስራ ተሰርቷል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply