You are currently viewing በህግ ማስከበር ሰበብ የታሰሩ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪዎችና አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የጦር መኮንኖችና ሲቪል ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ሲል አለን! ዓለም አቀፍ የአማራ ማ…

በህግ ማስከበር ሰበብ የታሰሩ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪዎችና አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የጦር መኮንኖችና ሲቪል ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ሲል አለን! ዓለም አቀፍ የአማራ ማ…

በህግ ማስከበር ሰበብ የታሰሩ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪዎችና አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የጦር መኮንኖችና ሲቪል ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ሲል አለን! ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ሕብረት ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ አለን! ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ሕብረት በአማራ ላይ ያነጣጠሩ ጭፍጨፋዎችንና ማፈናቀሎችን አስመልክቶ ‹ከአለን!› ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ሕብረት የተሰጠ ሙሉ መግለጫ:_ ‹‹አማራን ሀገር አልባ ለማድረግ በተናበበ መልኩ የተጀመረውን ዘመቻ እንመክት›› “አማራን ሀገር አልባ ለማድረግ በተናበበ መልኩ የተጀመረውን ዘመቻ እንመክት›› ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በተለያዩ ደረጃዎች የሚገለጹ አማራ ተኮር ግድያዎች፤ ማፈናቀሎች፤ የሃብት ንብረት ዝርፊያዎችና ውድመቶች የተፈጸሙት አማራን ጠላት አድርገው በፈረጁ እጅግ የተናበቡ ጠላቶች መሆኑ የሚታመን ሲሆን አማራን መግደል መደበኛ ስራ እስከሚመስል ድረስ ድርጊቱ መዋቅራዊና ስርዓታዊ ድጋፎችን አግኝቶ በተለይ ከአራት ዓመታት ወዲህ አሰቃቂ ጅምላ ጭፍጨፋዎች ተፈጽመዋል፡፡ በቤኒሻንጉል መተከልና ካማሺ ዞኖች በአማራ ላይ የደረሰው የዘር ፍጅት አማራ የተባለ ሁሉ የሰውነት ክብርን ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ እንደ እንስሳ በቀስት ሲታደን እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ፤ በሰሜን ሸዋ አጣዬና አካባቢው፤ እንዲሁም የተለያዩ ክስተቶችን የወዲያው ምክንያት ያደረጉ በወርሃ ጥቅምትና ሰኔ 2012 ዓ.ም ኦሮሚያ ተብሎ በተካለለው የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ ምስራቅ ሸዋ፤ አርሲ፤ ባሌ፤ ሀረርጌና ሌሎች ዞኖች በአሰቃቂ ሁኔታ የተፈጸሙ አማራ ተኮር ግድያዎች በሀገሪቱ በተፈጠሩ ደራሽና ተደራራቢ የፖለቲካ ሁኔታዎች ጅምላ ግድያዎቹ ከአንድ ሰሞን አጀንዳ ማለፍ እንዳይችሉ ማድረጋቸው ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ ነው፡፡ በየጊዜው የሚፈጸሙት አማራን ኦሮሚያ ተብሎ ከተካለለው ክልል የማጽዳትና አንገት አስደፍቶ ሀገር አልባ የማድረግ አስነዋሪ ስራዎች በተለያየ ሁኔታ የሚገለጹ ቢሆንም በማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ሊወገዙ በሚገባቸው አውዶች ነፍሰጡሮችን፤ አራስ እናቶችን፤ ጨቅላ ህጻናትንና አዛውንቶችን መርጦ እስከሚመስል ድረስ በጅምላ የገደሉ አካላት የአረመኔነትን ጥግ አሳይተዋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የተፈጸመው አማራ ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ግድያ እስከ አሁን የአስክሬን ስብሰባው ባለመጠናቀቁ የሟቾችን ትክክለኛ ቁጥር ማወቅ ባይቻልም የዐይን እማኞች ግን የሟቾች ቁጥር ከ1700 (አንድ ሺህ ሰባት መቶ) መሻገሩን አረጋግጠዋል፡፡ በአግላዩ የፖለቲካ ስርዓት መከራና ግፍን መቀበል የተፈረደባቸው ወገኖቻችን ገላቸው በስለት ሲሞሸለቅ፤ ህጻናት በጥይት አረር ሲቆሉ፤ አራስና ነፍሰጡር እናቶች በእሳት ሲቃጠሉ፤ ሚስኪኑ አርሶ አደር ባቀናው ቀዬ ላይ ሲገደልና ሲፈናቀል፤ በህይወት መኖሩ ብቻ ሳይሆን ሞቶም በክብር መቀበሩ ቅንጦት ሲሆንበት ለወደ ፊት የታሰበው እየሆነ ካለው የሚብስ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በወለጋ ጊምቢ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ሀገር እመራለሁ በሚለው ስርዓት የወጡ ጥቃቱን የሚያወግዙ የመግለጫ ጋጋታዎች ቀድሞውኑ ጥቃቱ ሊፈጸም እንደሚችል እያዩ ከማለፍ ጋር የሚጋጩ ሽሙጦችና ‹አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም› ብሂልን ስጋ የሚያለብሱ ናቸው፡፡ ይልቁኑም በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ማለትም በሰሜን ሸዋ ደራ ወረዳ፤ በምዕራብ ሸዋ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተፈጸመው ያሉ አማራና የማፈናቀል መጠነ ሰፊ ዘመቻዎች ከገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት አቋም ጋር ሲቀናጅ ይህ አማራን ሀገር አልባ የማድረግ ተግባር ለአዲስ አበባ ከተማ አማራዎች ሳይቀር የተደገሰና የማይቀር መሆኑ የተሰወረ አይደለም፡፡ በተለይም የገዢው ፓርቲ መሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከዚህ በፊት ‹በአዲስ አበባ ዙሪያ መሪያችን ተነካ ያሉ ወጣቶች ወደ አራት ኪሎ ሊመጡ ነበር› ባሉበት አንደበታቸው ሰሞኑን በፓርላማ ቀርበው ‹በአዲስ አበባ ኦሮሞ ጠል ሃይሎች አሉ፤ በከተማዋ ተረኝነቱ ገና ነው› ሲሉ ከዚህም የባሰ ችግር እንደሚኖር ሃላፊነት የጎደለው የግጭት ቅስቀሳ ንግግር በማድረግ ስጋትን አጭረዋል፡፡ ሰሞኑን የወለጋውን ጅምላ ጭፍጨፋ ተከትሎ አዲስ አበባን ጨምሮ በጎንደር፤ በባህርዳር፤በደብረማርቆስና በወሎ ዩኒቨርስቲዎች በተማሪዎች የተሰማው ቁጣን የመግለጽ ተቃውሞ በአንዳንድ ከተሞች በፖሊስ አፈናና ብተና ቢደረግበትም በባህርዳር ከዩኒቨርስቲዎች አልፎ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ህዝባዊ ቁጣው መቀጣጠሉን የሚያረጋግጡ ተቃውሞዎች ተደርገዋል፡፡ ይህ ህዝባዊ ቁጣ በሌሎች የአማራ ከተሞችም እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል፡፡ በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተገለጹት ነጥቦች ተግባራዊ እስኪሆኑ ድረስ የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል አለን! አለም አቀፍ የአማራ ማሕበራት ሕብረት ጥሪውን ያቀርባል። 1) በመዋቅራቸው የዘር ፍጅት ማስፈፀማቸውን የቀጠሉት የብልፅግና ፓርቲ መሪ ዐቢይ አህመድና ኦሮሚያ የተባለው ክልል ዋና ሹመኛ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የእነሱ ግብረአበሮች የሆኑት ሹመኞች በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጠየቁ፣ እንዲሁም ሀገር መመራት አቅቶት ኢትዮጵያን ወደ አስከፊ ቀውስ የከተታት የዐቢይ አህመድ መንግስት ስልጣኑን ለቅቆ ለህዝብ እንዲያስረክብ፣ 2) የአማራ ክልል በተባለው የሀገሪቱ ክፍል የመንግስት ሹመት ላይ ያሉት ምስለኔ ባለስልጣናት በአጠቃላይ በህዝብ ላይ እየቀለዱበት ካለው ስልጣናቸው ተነስተው ሕዝቡ በጊዜያዊነት በሚወክላቸው የአደራ አስተዳደር እንዲያስረክብ፣ 3) በመላው ኢትዮጵያ በየትኛውም አካባቢ የሚገኝ አማራ በተጠናከረና በተናበበ መልኩ በመደራጀት ራሱን ከየትኛውም ጥቃት እንዲከላከልና እንዲጠብቅ፣ 4) ምሁራን፣ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆነ ማንኛውም የሲቪክ ማህበራት በዚህ ወቅት ከዐቢይ አህመድም ሆነ ከአጋሮቻቸው ጋር ሊያደርጉት ከሚችሉት ፍፁም ተቀባይነት ከሌለው ውይይትም ሆነ ምክክር የማድረግ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ፣ 5) በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው በመንግስት የተደገፈ ሽብርና እልቂትን ለማስቆም ሲባል ህዝባዊ እምቢተኝነትና ብሄራዊ አድማ እንዲደረግ፣ 6) ህግ የማስከበር ዘመቻ በሚል የዳቦ ስም የወገን መከታ የሆነውን ፋኖን ትጥቅ በማስፈታት አማራን አንገት በማስደፋት የኦሮሙማን አጀንዳ ለማስፈፀም የሚካሄደው ዘመቻ በአማራ ህዝብ ላይ ዘር ጭፍጨፋ(ጄኖሳይድ) ለመፈፀም ታቅዶ ስለሆነ ድርጊቱ ባስቸኳይ እንዲቆምና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ 7) በህግ ማስከበር ሰበብ የታሰሩ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪዎችና አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የጦር መኮንኖችና ሲቪል ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ አማራ የማንነቱ መጠሪያ የሆነውን ስም እንዲሁ እንዳላገኘው ሁሉ ዛሬም ነጻ ሕዝብነቱን የሚያረጋግጠው በችሮታ ሳይሆን በትግል በመሆኑ ከሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን የአማራም ሆነ በሀገሪቱ የሚኖር የሁሉም ብሄረሰብ ሕልውና እስኪረጋገጥ እና በኢትዮጵያ ፍትህ እስኪሰፍን ድረስ ትግላችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን ለወዳጅም ለጠላትም እያሳወቅን የተጀመረው ትግል ሕዝባዊነቱን ይዞ እንዲቀጥል ጥሪ እናደርጋለን። ለመላው አማራ ሕዝብ በአማራነትህ እየተፈጸመብህ ስላለው መጠነ ሰፊ ጥቃት ነጋሪ ባያሻህም ስንት አማራ ሲሞት ግድያው እንደሚቆም አይታወቅምና በመዘናጋት ከሚከፈሉ መስዋዕትነቶች ለመጠበቅ በተጠንቀቅ ላይ እንድትሆን ማህበራችን በድጋሜ ያሳስባል፡፡ አማራ በመሆንህ እስከአሁን ያልተገደልከው በግድያው ስፍራ ስላልተገኘህ ብቻ መሆኑን በመረዳት የተራ ጉዳይ እንጂ ጊዜና ቦታ ጠብቀው ሊያጠፉህ እንደቋመጡ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የገጠመህን የህልውና ትግል ለማሸነፍና እስከዛሬ ከተፈጸመብህ በላይ ከታቀደልህ ማንነት ተኮር ፍጅት ለመዳን ከአንድ ሰሞንና ከማህበራዊ ሚዲያ ጊዜያዊ ተቃውሞ ተላቅቀህ ዘላቂና መሬት የወረደ ህዝባዊ የተግባር ትግልህን እንድትቀጥል ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ለመላው አማራ ወጣቶች የየትኛውም ህዝባዊ ትግል ዋና ሞተር ወጣቱ ኃይል ሲሆን ለህልውናው የማይደራደረው የአማራ ወጣትም ከዚህ ቀደም የትግል ፋናወጊነቱን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በመሆኑም በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተጀመረውን ይፋዊ ተቃውሞና እምቢተኝነት በቀጣይም ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጭምር የማሸጋገር፣ እንዲሁም ይህንን አማራ ጠል ስርዓት በማስወገድ ህልውና የማስጠበቅ ትግሉን ወጣቱ ሃይል በግንባር ቀደምነት የመምራት ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን። ለምሁራን “ሀገር ከአላዋቂዎች ንግግር ይልቅ በአዋቂዎች ዝምታ ትጠፋለች” እንዲል ብሂሉ በምሁራን ዘንድ የሚስተዋለው ዝምታን የመምረጥ አካሄድ እጅጉን አስፈሪ ሆኗል፡፡ ከሀገር አፍራሾች ዓላማቸውን ለማሳካት በዚህ ደረጃ ተናብበው ሌት ተቀን በሚሰሩበት ሁኔታ የተማረው ሃይል ነገሮችን ጆሮ ዳባ ብሎ ከማለፍ ይልቅ ህዝብን ከግድያ ሀገርን ከመበተን መጠበቅ ይቻል ዘንድ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲጫወቱና በእጃቸው ያለውን ታሪካዊ ሃላፊነት እንዲወጡ ማህበራችን ጥሪ ያስተላለፋል፡፡ በአዲስ አበባና ዙሪያው ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በ2011 በቡራዩ በሰበታና በሌሎች የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች የተፈጸሙ ማንነት ተኮር ግድያዎች ይህ አደገኛ ሃይል አናሳ ያላቸውን ሁሉ ሰልቅጦ የመዋጥ ፍላጎቱን ፍንትው አድርገው ያሳዩ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም በኦሮሚያና አዲስ አበባ የሚገኙ ብሄሮች የዚህ ሃይል አስፈሪ አካሄድ ከዚህ በፊት የታዩ ጥቃቶችና አብሮነትን የሚሸረሽሩ አስነዋሪ ድርጊዎች በባሰ ሁኔታ ሊፈጸሙ እንደሚችሉ የሚገመት በመሆኑ ራሳቸውን እንዲጠብቁና እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በንቃት እንዲከታተሉ እናሳስባለን፡፡ አለን! ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ሕብረት ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ/ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply