You are currently viewing ##በህግ ማስከበር ስም አቅም ያላቸውን የአማራ ልጆች የማሳደድ ተግባር! ሰ.አሜሪካ:- ግንቦት 19/2014 ዓ.ም          አሻራ ሚዲያ ደግ አረግ ዋለ የደብረ ማርቆስ…

##በህግ ማስከበር ስም አቅም ያላቸውን የአማራ ልጆች የማሳደድ ተግባር! ሰ.አሜሪካ:- ግንቦት 19/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ደግ አረግ ዋለ የደብረ ማርቆስ…

##በህግ ማስከበር ስም አቅም ያላቸውን የአማራ ልጆች የማሳደድ ተግባር! ሰ.አሜሪካ:- ግንቦት 19/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ደግ አረግ ዋለ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ መምህር ነው። በደብረ ኤልያስ ወረዳ የአብን አባል እና የምርጫ እጩ ተዋዳዳሪ ነበር። መምህር ደግ አረገ ያመነበትን ፊት ለፊት የሚናገር፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለወገኑ ድምጽ የሚሆን ንቁ አማራ ነው። በእዚኽ ባሕሪውም በተለያዩ መድረኮች የብልጽግናን አስተዳድር አምርሮ ይነቅፋል። በምርጫ 2013 በተለያዩ ጣቢያዎች እየተዘዋወረ የምርጫ ኹነቱን ሲመለከት፣ የከተማ አስተዳደሩ ኢንቨስትመት መምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ትዕግስት የኔ አባት ድምጽ ለመስረቅ እና ኮሮጆ ለመገልበጥ ስትሞክር ደርሶባት ጉንጭ አልፋ ንግግር ተነጋግረው እንደ ነበር እና ወ/ሮ ትዕግስትም ለበቀል ስትፈለግው ነበር። መምህር ደግአረገ፤ የደብረ ማርቆስ ቤቶች ማኅበረ ከመረጣቸው 20 የኮሚቴ አባላት ውስጥ አንዱ በመሆን ሲያገለግል ነበር። በዚህ ሂደትም፤ የቤቶች ማህበር ቦታ አሰጣጡ እንዲዘገይ ሆነ ብሎ ከሚሠራው ከከንቲባው ከአቶ ይትባረክ አውቀ ጋር ፊት ለፊት ሲገጥም እና ሲከራከር ነበር። በዚህ ቂም ያረገዘው አቶ ይትባረክ በተለያዩ ስብሰባዎች “አብን” እያለ ለማሸማቀቅ ሲሞክር ነበር። አቶ ይትባረክ እና ወይዘሮ ትዕግስት ለግል ቂም ማስተንፈሻቸው፤ የሰሞኑን “ህግ ማስከበር” የሚል የዳቦ ስም ተጠቅመው እንዲታፈን አድርገዋል። ወደ የትኖራ በመውሰድ ሌሊት ሌሊትም ድብደባ እየፈጸሙበት ይገኛሉ። ፍትህ ለደጋረገ ዋለ

Source: Link to the Post

Leave a Reply