You are currently viewing “በህግ ማስከበር ስም የአማራ ህዝብን ለማንበርከክ የሚደረገው አፈና፣ እገታና ግድያ ኢትዮጵያን ያፈርሳታል”!  እኛ በመላው በአውስትራልያ የምንገኝ የአማራ ህዝብ ሲቪክ ማህበራት በኦሮሞ ብልፅ…

“በህግ ማስከበር ስም የአማራ ህዝብን ለማንበርከክ የሚደረገው አፈና፣ እገታና ግድያ ኢትዮጵያን ያፈርሳታል”! እኛ በመላው በአውስትራልያ የምንገኝ የአማራ ህዝብ ሲቪክ ማህበራት በኦሮሞ ብልፅ…

“በህግ ማስከበር ስም የአማራ ህዝብን ለማንበርከክ የሚደረገው አፈና፣ እገታና ግድያ ኢትዮጵያን ያፈርሳታል”! እኛ በመላው በአውስትራልያ የምንገኝ የአማራ ህዝብ ሲቪክ ማህበራት በኦሮሞ ብልፅግና መሪነትና በአማራ ብልፅግና ገበቴ አቃፊነት በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ህገወጥ እገታ፣ እስር፣ ድብደባና ግድያ በእጅጉ አጥብቀን እንቃወማለን። በረዥም ዘመናት የኢትዮጵያ የታሪክ ኑባሬ የአማራ ህዝብ የሀገርን ክብርና ልዕልና ከፍ ለማድረግ መስዋዕትነትን ሲከፍል ኖሯል፤ አሁንም እየከፈለ ይገኛል። በቅርቡ እንኳን የሀገር መከላከያ የሰሜን ዕዝ በህወሓት በ45 ደቂቃ ኦፕሬሽን ከጥቅም ውጭ ሲሆንና ህወሓት ሀገርን ለማፍረስ ” ቁርስ ጎንደር፣ ምሳ ባህርዳር” ብሎ ለወረራ ሲገሰግስ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ቀራቅርና ዳንሻ ላይ ወራሪውን አከርካሪውን ሰባብ…ሮ የመለሰው መሆኑና ህወሓት በዳግም ወረራ እስከ ደብረ-ብርሀን ሲመጣ የአማራ ህዝብ በልዩ ሀይሉ፣ ፋኖውና ሚሊሻ ወራሪውን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ የመለሰበት የቅርብ ጊዜ ለሀገር አንድነትና ሰላም አማራ የከፈለው ደማቅ ታሪኩ ነው። ይህም ሆኖ የኦሮሞ ብልፅግና በበላይነት የሚመራው “መንግስት” ይህንን የአማራ ህዝብ መስዋዕትነት ጥላሸት በመቀባት የህዝባችንን የድል ስሜት ከመንጠቅ ባለፈ በታቀደ ሁኔታ የአማራ ጦር መሪዎችን፣ ጀብዱ የሰሩ ወታደሮችን፣ እና ህዝባዊ የፋኖ አመራሮችን ከእውቅናና ሽልማት ውጭ አድርጓቸዋል። ይባስ ብሎ የአማራ ጦር መሪዎችን፣ የልዩ ሀይል አባላትን፣ የፋኖ አመራሮችንና አባላትን፣ ህዝባዊ የአማራ ምሁራንንና አንቂዎችን፣ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ማገት፣ ማሰርና መሰወርን በስፋት አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ስለሆነም እኛ በመላው አውስትራሊያ ፣የምንገኝ የአማራ ሲቪክ አደረጃጀቶች የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል። ፩. ለኢትዮጵያ ፌደራል “መንግስት” የፌደራል መንግስት አቋም-የለሽ፣ አስመሳይና አሳሳች በሆነ አካሄዱ ሀገርና ህዝብን ሰላምና ግዛታዊ አንድነታቸውን ማስከበር አልቻለም። የህዝብ መፈናቀል፣ መጎሳቆልና ሞት እንዲሁም ርሀብ በመላው የሀገራችን ክፍል ተንሰራፍቷል። ስለሆነም በአስቸኳይ የሽግግር ጊዜ ባላደራ መንግስት እንዲቋቋምና የፌደራል መንግስቱ ስልጣኑን እንዲያስረክብ እንጠይቃለን!!! ፪: ለአማራ ክልል መንግስት የአማራ ክልልን እያስተዳደረ ያለው የአማራ ብልጽግና ከጥንተ-ተፈጥሮው የተጣባውን ተላላኪነትና ተምበርካኪነቱን ማቆም አልቻለም፤ የማቆም ፍላጎትም የለውም። ወራሪው የህወሓት ጦር ደብረታቦርን ለመያዝ የሞትሽረት ትግል ሲያደርግ የአማራ ክልልን ሲመሩ የነበሩ አመራሮች የህዝቡን ገንዘብ ተከፋፍለውና ሻንጣቸውን ሸክፈው ፍርጠጣ ላይ የነበሩ ቢሆንም የወራሪው ሀይል በአማራ ህዝብ ትግል ተቀልብሶ ወራሪው ወደጎሬው ሲመለስ እኒሁ ፈርጣጭ አመራሮች ተመልሰው መሾምና መሸለማቸው ሳያንስ ለአማራ ህዝብ ከፍተኛ መስዋዕትነትን የከፈሉ የጦር መሪወችን፣ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ አመራርና አባላትን፣ የህዝብ ውግንና ያላቸው የፖለቲካ አመራሮችንና ጋዜጠኞችን ማፈን፣ ማሳደድና መግደል ጀምረዋል። ይህ እጅግ አደገኛ የሆነ የውንብድና አካሄድ በአስቸኳይ እንዲቆም እናስጠነቅቃለን። በተለያዩ የክልሉና ከክልሉ ውጭ ታፍነውና ታግተው የሚገኙ የጦር መሪወች፣ የልዩ ሀይል፣ ፋኖና ሚሊሻ አመራሮችና አባላት፣ የፖለቲካ አመራሮችና ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እንጠይቃለን። እንዲሁም የክልሉ መንግስት የመንግስትነት ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ ስላልሆነ እና የህዝባችንን የግዛትና ማንነት አንድነትን ማስጠበቅ ስላልቻለ በአስቸኳይ የባለሙያወች የባላደራ መንግስት እንዲቋቋምና የአማራ ብልጽግና ስልጣኑን እንዲያስረክብ እናሳስባለን!!! ይህ የማይሆን ከሆነ ህዝባችንን በማስተባበር በህዝባዊ ሰላማዊ እምቢተኝነት የምናካሂድ መሆኑን እናስጠነቅቃለን!!! ፫: ለአማራ ልዩ ሀይል፣ ፖሊስ፣ ፋኖና ሚሊሻ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻና ፋኖ የማይነጣጠሉ የአማራ ህዝብ የሰላምና ደህንነት መሰረቶቹ ናቸው። በጭንቁ ጊዜ ኮቾሮ በልተው፣ በአንድ ኮዳ ውሀ ጠጥተው፣ በአንድ ምሽግ ውስጥ ከጠላት ጋር የተዋደቁ ለአማራ ህዝብ ሰላምና ደህንነት ደማቸውን ያፈሰሱ፣ አጥንታቸውን የከሰከሱ መመኪያወቻችንና ኩራቶቻችን ናቸው። ስለሆነም በመንግስት አደረጃጀት ውስጥ ያላችሁ ልዩ ሀይሎቻችን፣ ፖሊስና ሚሊሻወቻችን በኦሮሞ ብልጽግና ፊታውራሪነት እየተመራ ባያለው አፈናና እገታ ባለመሳተፍ ከወንድምና እህቶቻችሁ ፋኖወች ጋር እንድትቆሙ ስንል በአፅንዖት እናሳስባለን። ፋኖ ከአውራጃ አደረጃጀቶች ባለፈ በአስቸኳይ ወጥ ወደሆነ አደረጃጀት እንዲደራጅ እያሳሰብን ይህ አደረጃጀት ፋኖን በቋሚነት ለማገዝና ለማደራጀት የሚሠሩ ስራዎችን በቀላሉ ያሳልጣል። ለዚህ አደረጃጀት ሂደት አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ እገዛ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንንም እንገልጣለን። ፬: ለአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አብን ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበትና አብዛኛው የአማራ ህዝብ በተስፋ የሚያየውና የመታገያ ሜዳ አድርጎ የሚወስደው የአማራ ብሄርተኝነት አምጦ የወለደው ልጁ እንደሆነ እሙን ነው። ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከብልጽግና መንግስት ሹመትን ተቀብለው እየሰሩ ያሉ አመራሮች ከህዝብና ከጠቅላላ ጉባዔው ፍላጎት እንዲሁም ከፓርቲው መተዳደሪያ ህገ ደንብ ውጭ የሆኑ ውሳኔወችንና አካሄዶችን ሲያደርጉና በዚህም አብዛኛውን የንቅናቄውን አባልና ደጋፊ ሲያሳዝነው ተመልክተናል። ስለሆነም የምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በማካሄድ ውግንናቸው ለአማራ ህዝብ የሆኑና ለአማራ ህዝብ የፍትህ፣ የነጻነት፣ የግዛትና የማንነት ጥያቄወች የታመኑ አመራሮችን በመምረጥ አብን ወደነበረበት ከፍታ እንዲመልሱ ስንል እንጠይቃለን። ለዚህ ተግባርም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የምናደርግ መሆኑን ጭምር እንገልጣለን። ፭. ለአማራ ዲያስፖራ የአማራ ዲያስፖራ ለኢትዮጵያ አንድነትና ልማት የጀርባ አጥንት ሆኖ የዘለቀ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በአሁኑ ጊዜ ወቅቱ የሚጠይቀውን የፖለቲካ አሰላለፍ መከተል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ሀገር ቤት ያለው የአማራ ህዝብ እጅግ ግዙፍ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና የህልውና ችግሮች ተጋርጠውበታል። ይህንን አደጋ ለመቀልበስ የአማራ ዲያስፖራ ጊዜህን፣ ገንዘብህንና እውቀትህን ለአማራ ህዝብ እንድታውል እናሳስባለን። የአማራ ተቋማትን አግዝ፤ ፋኖን አጠናክር፤ የአማራ ህዝብን በደልና መከራ ለአለማቀፉ ማህበረሰብ አሳውቅ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን!!! አማራ በልጆቹ ትግል ያሸንፋል!!! በአውስትራሊያ የአማራ ሲቪክ ማህበራት፣ 1. የደቡብ አውስትራሊያ የአማራ ህዝብ ማህበር (Amhara Association In South Australia) 2. ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (Moresh Wegenie Amhara Organization) 3. በሚልበርን፣አውስትራሊያ የአማራ ማህበር (Amhara Association in Melbourne, Australia) 4. የኢትዩ-አውስትራሊያን የሰብአዊይ፣የእድገትና፣የሰላም ግንኙነት ማህበር (Ethio-Australian Humanitarian, Development, Peace program interconnection Inc) 5. በኩይንስላንድ የአማራ ህዝብ ማህብር (Amhara Association In Queensland, Australia) 6. በአውስትራሊያ፣ የወልቃይት የአማራ ማህብር (Welkait Amhara Association in Australia)

Source: Link to the Post

Leave a Reply