በህግ ማስከበር ዘመቻው በሽሬና መቐለ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ30ሺ በላይ ኩንታል እህል ድጋፍ ማድረጉን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለአሀዱ እንደገለፁት በመቐለ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ12 ሺ በላይ፤ በሽሬ ደግሞ ከ18 ሺ በላይ ኩንታል እህል ድጋፍ ተደርጓል፡፡ድጋፍ በጊዜያዊ አስተዳደሩ በኩል ተደራሽ መደረጉን አቶ ደበበ ገልጸው የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአስተባባሪነት ከውሀ መስኖና ኢነርጂ፣ ከሴቶች ህጻናትና ወጣቶች እና ከግብርና ሚኒስቴር ኮሚቴዎች ተውጣጥተው ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ገልጸዋል፡፡በጊዜያዊ መጠለያ ማዕከል ውስጥ ያሉ ዜጎች ለበሽታ በመጋለጣቸው መድሀኒት ከማቅረብ ጀምሮ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን በሟሟላት ኮሚሽኑ በትኩረት እየሰራ መሆኑም ተገልጻል፡፡በተፈጠረው ግጭት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በቀጣይ ወደ ቀድሞ ስፍራቸው ለመመለስ እደሚሰራ ነው የተገለጸው፡፡

ቀን 12/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply