በህግ ከለላ ስር የሚገኙት የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች የፍርድ ቤት ዉሳኔ ለግንቦት 17 እንደገና መቀጠሩ ተነገረ፡፡

የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች የፍርድ ቤት ዉሳኔ እንደገና ለግንቦት 17 ቀጠሮ መሰጠቱ የተገለፀ ሲሆን አመራሮቹ በማረሚያ ቦታዎች እንዲሟላላቸዉ ጠይቀዋቸዉ የነበሩ የመንፈሳዊ ክንዋኔ ማስኬጃ ጥያቄዎች የማረሚያ ቤቱ ሀላፊ ቀርበዉ በሰጡት ምላሽ ሳይፈቀድላቸዉ መቅረቱ ተገልፃል፡፡

የእምነት ክንዋኔ ማስኬጃ ቦታዎች እንዲሟሉላቸዉ የሚፈልጉ ከሆነ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት መዛዎር እንዳለባቸዉ በፍርድ ሂደቱ ወቅት መገለፁ ተነግሯል፡፡በማረሚያ ቤት የሚገኙት የፓርቲዉ አባላት በምርጫ እንዲሳተፉ ለማድረግ ፓርቲዉ ምርጫ ቦርድን ከሶ የነበረዉን ዉሳኔም ምርጫ ቦርድ ለሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረበዉ መልስ ምክንያት እንደገና ለምርጫ ቦርድ ፓርቲዉ መልስ እንዲያቀርብ ዉሳኔ በመተላለፉ መልሳችንን በፅሁፍ እናቀርባለን ሲሉ የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶክተር በቃሉ አጥናፉ ለአሐዱ ተናግረዋል ፡፡

ቀን 10/09/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post በህግ ከለላ ስር የሚገኙት የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች የፍርድ ቤት ዉሳኔ ለግንቦት 17 እንደገና መቀጠሩ ተነገረ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply