በህግ ጥበቃ ለማያገኙ ድምፅ አልባ ሰራተኞች የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ተጠየቀ::

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) ይህንን ጥሪው ያቀረበው የተጋላጭ ሠራተኞችን መብቶች የሚያስጠብቁ የዓለም ሥራ ድርጅት ኮንቬንሽኞች እንዲጸድቁ ለማስቻል በጠየቀበት መድረክ ነው።

ኮንቬንሽን 189፣ 190፣ 97 እና 143 ለተጋላጭ የቤት ሠራተኞች፣ ፍልሰተኛ ሠራተኞች፣ እና በሥራ ቦታ ጥቃት እና ትንኮሳ ሰለባዎችን ለማስቀረት ኮንቬንሽኖቹ በኢትዮጵያ የህግ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲገቡ የተጠየቁት ኮንቬንሽኖች ናቸው።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ የዚህ ዘመቻ አላማ በሰራተኞች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እና ሰለባዎችን በጋራ ለማስቆም ያለመ እንደሆነ አንስተው ፣ የኮንቬንሽኖቹ መፅደቅ ፍትሃዊ እና ክብር ያለው የሥራ ቦታ ለመፈጠር ትልቅ ሚና እንዳለውም አንስተዋል።

አቶ ካሳሁን ጨምረውም በሀገራችንም ይሁን በፍልሰተኞች ላይ ላሉ የቤት ሰራተኞች የሚሰጠውን አመለካከት እንዲሁም የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመቀነስ ከኮንቬንሽኖቹ መፅደቅ ባለፈ ሁሉም ማህበረሰብ የድርሻውን እንዲወጣም ተጠይቋል።

የዚህ ኮንቬንሽን መፅደቅ በኢትዮጵያ ያሉትን ጨምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የቤት ሠራተኞች መሠረታዊ መብቶችን ለማረጋገጥ፣ የቤት ውስጥ ሥራ ስምሪት በማስተካከል ፍትሃዊ በማድረግና ሰብአዊ ክብር ለማላበስ የተቀረጸ በመሆኑ መንግሥት ተቀብሎ እንዲያጸድቀው ተጠይቋል፡፡

የፌዴራል የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ 1156/2011 የቤት ሠራተኞችን ከወሰኑ ውጪ ያደረገና ያለ ሕግ ከለላ የተዋቸው በመሆኑ ይህ እንዲሻሻልም ተጠይቋል።

መንግስትን ወክለው የተገኙት ዶር ተካልኝ አያሌው በስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ተወካይ የተጠየቀው ኮንቬንሽን እንዲፀድቅ ጉዳዩን እንደሚያቀርቡም ተናግረዋል።

በለዓለም አሰፋ

የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply