#በህጻናት ላይ የሚከሰት #ትንታ ባዕድ ነገር ወደ መተንፈሻ ቱቦ ሲገባ የሚከሰት እክል ትንታ እንደሚባል ተነግሯል፡፡ ትንታ በአዋቂዎች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በህጻናት ላይ ግን በተደጋጋሚ የሚ…

#በህጻናት ላይ የሚከሰት #ትንታ

ባዕድ ነገር ወደ መተንፈሻ ቱቦ ሲገባ የሚከሰት እክል ትንታ እንደሚባል ተነግሯል፡፡ ትንታ በአዋቂዎች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በህጻናት ላይ ግን በተደጋጋሚ የሚከሰትበት ሁኔታ አለ፡፡

በመተንፈሻ ቱቦ ምግብም ሊሆን ይችላል ማንኛውም ባዕድ ነገር ሲገባ እና ሰውነት በተፈጥሮ የገባውን ባዕድ ነገር ለማውጣት በሚፈጥረው ጥረት ትንታ ይከሰታል።

ዶክተር ብስራት ጌታቸው ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት ናቸው፤ በህጻናት ላይ በድንገት ማንኛውም ባዕድ ነገር ወይም ወደ ምግብ ቱቦ መግባት የነበረበት ምግብ አልያም መጠጥ ወደ መተንፈሻ ቲቦ ሲገባ ትንታ የሚከሰት መሆኑን ነግረውናል፡፡

#ምክንያቶች

• ህጻናት መጫዎቻዎችን ወደ አፋቸው በማስገባት በሚፈጥር መዋጥ እና ወደ አየር ቱቦ መገባት
• ምግብ ቶሎ ቶሎ እንዲመገቡ ከተደረገ

#ምልክቶች

• በዋነኛነት ሳል ይከሰታል
• ለመተንፈስ መቸገር
• ሲተነፍሱ ድምጽ ማሰማት
• መረበሽ፣ የመደንገጥ ስሜት መኖር
• ማቃሰት
• በሰዓቱ ኦክስጂን ስለሚያጡ የከንፈር መጥቆር
• የጣት መጥቆር
• እጅን ወደ አፋቸው እና ጉሮሮ መክተት
• እንዲሁም ህጻናት ወደ ጉሮሮ የገባውን ባዕድ ነገር ለማውጣት መሞከር ይስተዋላል።

#ትንታን ለመከላከል

• ህጻናቱን ትንሽ ትንሽ መመገብ
• በአፋቸው ምግቡን እያላሙጡ እንዲውጡ ማድረግ
• በተቻለ አቅም ህጻናት ከወላጆች አከባቢ እንዲርቁ አለመፍቀድ
• ወላጆት ህጻናት ሲጫዎቱ መከታተል እና ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ።

#ትንታው ካጋጠመ ምን ማድረግ ይመከራል?

በህጻናት ላይ ትንታ ሲያጋጥም በቅድሚያ ወላጆች ወይም በህጻናቱ አከባቢ ያሉ ሰዎች ሊረጋጉ ይገባል ብለዋል፡፡

• ህጻናቱ እንዲያስሉ እና የገባውን ባዕድ ነገር ወይም ምግብ እንዲወጣ መፍቀድ
• አፍንጫን አለመያዝ

#ህክምናው

የህጻናቱን ሰውነታቸውን ገልብጦ በክርናችን ትዩዩ በማስቀመጥ በጭናችን ላይ ማስደገፍ፤ አገጫቸውን እና ከአንገታቸውን ዝቅ በማድረግ በጀርባቸው በኩል ከአንገታቸው ትንሽ ዝቅ በማለት 5 ጊዜ በመጠኑ መምታት ወደ አየር ቱቦ የገባውን ባዕድ ነገር ወይም ምግብ እንዲወጣ ይረዳል ተብሏል፡፡

ነገር ግን የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጡ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ባለሞያው ተናግረዋል፡፡

#በእሌኒ ግዛቸው
ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply