በሆሮጉዱሩ ወለጋ አባቦ ጉዱሩ በሚባል ልዩ ቦታ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቃዎች በንጹሀን ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተሰማ።   (  አሻራ ጥር፡-14/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር) ሆሮጉዱሩ ወለጋ…

በሆሮጉዱሩ ወለጋ አባቦ ጉዱሩ በሚባል ልዩ ቦታ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቃዎች በንጹሀን ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተሰማ። ( አሻራ ጥር፡-14/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር) ሆሮጉዱሩ ወለጋ…

በሆሮጉዱሩ ወለጋ አባቦ ጉዱሩ በሚባል ልዩ ቦታ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቃዎች በንጹሀን ላይ ጥቃት መፈጸማቸው ተሰማ። ( አሻራ ጥር፡-14/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር) ሆሮጉዱሩ ወለጋ የሚኖሩ አማራዎች ዛሬም ከፍተኛ ጥቃት እየተፈጸመባቸውና እየተፈናቀሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡… በዛሬው ዕለትም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኦነግ ታጣቂዎች በንጹኀን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ እንደምንጫችን ገለጻ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ በምንኖር የአማራ ተወላጆች ላይ ብዙ ግፍና በደል እየደረሰብን ይገኛል ሲሉም ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ለተፈጠረውና እየተደረገ ላለው የዘር ማጥፋትና የማፈናቀል ወንጀል ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያሉ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ለአጥፊው ቡድን ተባባሪ እንደሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በወለጋ ለሚካሄደው የዘር ጭፍጨፋና ማፈናቀል እንዲሁም ለሚደርሰው እንግልት ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ግንባር ቀደም ተዋኒያን በመሆናቸው መንግስት ለህግ ማቅረብና ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡ በተጨማሪም በወለጋ የሚደረገውን ዘርን የማጥፋት ጥቃትና አጥፊዎችን መንግስት በችልተኝነት መመልከቱን ምንጫችን ኮንነዋል፡፡ ችግሩ በተፈጠረበት አካባቢ የሚኖሩ ንጹሀን ዜጎች ለሚመለከተው አካል ብናመለክትም እስካሁን ግን የደረሰልን የመንግስት አካል የለም የኦነግ ታጣቂዎችም ቤት እያቃጠሉ ንብረት እየዘረፉ ነው ሲሉ ምንጫችን ለአሻራ ሚዲያ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለንብለዋል፡፡ ስለሆነም መንግስት በአስቸኳይ አከባቢው ላይ መከላከያ እንዲገባ ማድረግ እንዳለበትና የዜጎችን ህይወት ማትረፍ እንዳለበት የአካባቢው ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply