You are currently viewing በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኦዳቡልቅ/ሰቀላ ላይ በነበረው በጥላቻ የተሞላ ቅስቀሳ አማራውን ከቀዬው ለማፈናቀል የዘመተው በልዩ ኃይሉ የተመራው ኦነጋዊ ኃይል በፈጸመው ጥቃት ከ5 በላይ አማራዎች ተ…

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኦዳቡልቅ/ሰቀላ ላይ በነበረው በጥላቻ የተሞላ ቅስቀሳ አማራውን ከቀዬው ለማፈናቀል የዘመተው በልዩ ኃይሉ የተመራው ኦነጋዊ ኃይል በፈጸመው ጥቃት ከ5 በላይ አማራዎች ተ…

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኦዳቡልቅ/ሰቀላ ላይ በነበረው በጥላቻ የተሞላ ቅስቀሳ አማራውን ከቀዬው ለማፈናቀል የዘመተው በልዩ ኃይሉ የተመራው ኦነጋዊ ኃይል በፈጸመው ጥቃት ከ5 በላይ አማራዎች ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ኦዳቡልቅ/ሆሮቡልቅ/ሰቀላ ላይ በነበረው በጥላቻ የተሞላ ቅስቀሳ አማራውን ለዘመናት ከሚኖርበት ከቀዬው ለማፈናቀል፣ለመግደል እና ለማሳደድ የዘመተው በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተመራው ኦነጋዊ ኃይል በፈጸመው ጥቃት ከ5 በላይ አማራዎች መግደሉ ታውቋል። ከኦዳቡልቅ በሬ እያረደ ከኦነግ ሸኔ አባላት ጋር ለሶስት ቀናት ሲመክር ሰንብቷል የተባለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ህዳር 12/2015 ታላቅ ሰልፍ እና ስብሰባ በማድረግ በጥላቻ የተሞላ ቅስቀሳ ሲያደርግ መዋሉ ተወስቷል። ይህን ቅስቀሳ ተከትሎ በማግስቱ ህዳር 13/2015 ንጋት ላይ ከኦዳቡልቅ የተነሳው በብዙ ሽህ የሚቆጠረው ኃይል ወደ:_ 1) በኦዳቡልቅ ሰምቦ ለጋ ፈርሶ ቀበሌ እና 2) በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኪቲቻ ቀበሌ ይፋዊ ጦርነት ከፍቶ ከ5 በላይ አማራዎችን ገድሏል። ቡድኑ በደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ በሀዘን ቤት ጭምር ዲሽቃ በመተኮስ አማራዎችን ሲገድል፣ በጃርዴጋ ሹልኬ በተባለ ኬላ አካባቢም 3 አማራዎችን በድምሩ ከ5 በላይ ነዋሪዎችን በግፍ ስለመግደሉ የዐይን እማኞች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል፤ አንዳንዶች የሟቾችን ቁጥር 8 ያደርጉታል። ይህ የተሰባሰበ ኃይል በሰምቦ ለጋ ፈርሶ ቀበሌ 10 የሚሆን የአርሶ አደር ቤቶችን አቃጥሏል። በግፍ ለተገደሉት አማራዎች መካከልም:_ 1. ሰይድ አለም፣ ከአሁን በፊት አባቱ አቶ አለም ይብሬ እና አጎቱ ቃሲም ይብሬ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በግፍ የተገደሉበት ሲሆን እሱም ለ7 ወራት በኦህዴድ እስር ቤት ሲሰቃይ የቆዬ ጀግና እንደነበር ተገልጧል። 2. ጦይብ አለም፣ 3. መሀመድ ጅብሪል፣ 4. አዳነ አሰፌ እና 5. ኢሳ አሕመድ ይጠቀሳሉ። በጥቃቱ ከቆሰሉት መካከልም:_ 1. አሕመድ ይመር፣ 2. ሐብቴ ስጦት፣ 3. ወርቁ በዜ እና 4.ደጉ መኮንን የተባሉ ነዋሪዎች ይገኙበታል። የሟቾች እና የቁስለኞች ቁጥር ከዚህ ሊያሻቅብ እንደሚችል፣ ከቆሰሉትም በህክምና እጦት የሞቱ ስለመኖራቸው ነው የአሚማ ምንጮች የተናገሩት። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከኦነግ ሸኔ ጋር መስማማቱ የሚታወቀው ህዳር 13/2015 አሸባሪው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን በማሰባሰብ ላይ በመሆናቸው በነዋሪዎች ላይ ሌላ የተደራጀ ጥቃት ሊፈጽሙ እንደሚችሉ ተጠቁሟል። የአሚማ ምንጮች እንዳሉት ደግሞ ህዳር 15/2015 መከላከያ ሰራዊት ወደ ሰቀላ እየገባ መሆኑን ተከትሎ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምሬሳ እና የአካባቢው መስተዳድር አካላት፣ አማራን አጽድተን ተመልሳችሁ ትገባላችሁ በሚል በኦነግ ሸኔ እንዲለቁ የተደረጉ የኦሮሞ ተወላጆችን በመሰብሰብ “አማራ አፈናቀለን” በሉ በማለት ሲያስጨንቁ መዋላቸው ተሰምቷል። ይህን ምክር የሰሙ በርካታ የጃርዴጋ ነዋሪዎችም በዞኑ እና በወረዳ መስተዳድሮች የተሳሳተ መረጃ እና ትዕዛዝ ዳግም የጥቃት ሰለባ እንሆናለን በሚል ስጋት ወደ ገጠር ቀበሌ ለመውጣት መገደዳቸው ተገልጧል። በጃርዴጋ ከተማ ሚኖሩ አማራዎች መስከረም 12፣ 14 እና ህዳር 13/2014 ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት ተደጋጋሚ ጦርነት ተከፍቶባቸው በርካቶች መገደላቸው ይታወቃል። በበርካታ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አካላት የስንቅ፣የትጥቅ እና መረጃ ድጋፍ ወረራ እየፈጸመ ባለው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን አባላት በኩልም ጉዳት የደረሰ መሆኑ አይዘነጋም። በመጨረሻም አሁንም ላይም በአካባቢው ከፍተኛ ስጋት ስላለ የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ እንዲደርስ ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply