You are currently viewing በሆሮ ጉድሩ ዞን አሙሩ ወረዳ በሀረር ጃርሶ ቀበሌ ከኦሮሞ ሚሊሻዎች ጥቃት በመሸሽ ከ84 በላይ አባዎራ እና እማዎራ አማራዎች ተፈናቀሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 11 ቀን 2013…

በሆሮ ጉድሩ ዞን አሙሩ ወረዳ በሀረር ጃርሶ ቀበሌ ከኦሮሞ ሚሊሻዎች ጥቃት በመሸሽ ከ84 በላይ አባዎራ እና እማዎራ አማራዎች ተፈናቀሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 11 ቀን 2013…

በሆሮ ጉድሩ ዞን አሙሩ ወረዳ በሀረር ጃርሶ ቀበሌ ከኦሮሞ ሚሊሻዎች ጥቃት በመሸሽ ከ84 በላይ አባዎራ እና እማዎራ አማራዎች ተፈናቀሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሆሮ ጉድሩ ዞን አሙሩ ወረዳ በሀረር ጃርሶ ቀበሌ ከኦሮሞ ሚሊሻዎች ጥቃት በመሸሽ ከ83 በላይ አባዎራ እና እማዎራ አማራዎች ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው ሀብት ንብረታቸውንና አዝመራቸውን ጥለው ተፈናቅለዋል። ዳውድ አህመድንና አብዲ አማን የተባሉ አማራዎችን በጳጉሜ 2013 በጦር እና በገጀራ ሀረር ጃርሶ ቀበሌ ላይ ከተፈፀመባቸው ጥቃት ሮጠው ማምለጣቸው ተነግሯል። ከአንድ ወር በፊት ወደ 20 የሚሆኑ የኦሮሞ ሚሊሻዎች ከሰለጠኑና ከታጠቁ በኋላ አሸባሪውን ኦነግ ሸኔን መቀላቀላቸው ተወስቷል። እነዚህ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው የከዱ ሚሊሾች ከመከኖ፣ ከሀረር ጃርሶ ቀበሌ እና በተለያዩ የአሙሩ ወረዳ ስር የሚገኙ ቀበሌዎች መንግስት መልምሎ ያሰለጠናቸው መሆኑ ተሰምቷል። በተጨማሪም ከጳጉሜ በፊት የሰለጠኑ 30 የኦሮሞ ሚሊሻዎች ከሰሞኑ ትጥቅ ተቀብለው ከመውረዳቸው በአማራዎች ሰፈር ላይ በመተኮስና በ በማስፈራራት ላይ መጠመዳቸውን ተከትሎ ለአሙሩ ወረዳ አስተዳዳሪ ለአቶ በላይ ችግሩ እንዲቀርፉት ጥሪ ቢደረግላቸውም መፍትሄ ሰጭ ባለመሆናቸው እና ልቀቁ በማለታቸው 84 አባዎራ እና እማዎራ በቀላሉ 420 አማራዎች ከቀያቸው ለመልቀቅ ተገደዋል ተብሏል። ተፈናቃዮችም ከሀረር ጃርሶ ተነስተው ወደ አሙሩ ጃቦ ደቦን፣ መከኖ እና ሰምቦዋቶ ቀበሌ መሸሻቸው ታውቋል። በጥቅሉ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ጀምሮ እስከ መስከረም 8 ቀን 2014 ከቀያቸው የተፈናቀሉ አባዎራና እማዎራ አማራዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ይቀርባል:_ 1) የኑስ እርገጤ፣ 2) ማሞ እርገጤ(ወንድማማች) 3) ካሳ ዳውድ 4) ክንዱ ጋሻው 5) መሀመድ ሀሰን 6) አማን ሰይድ 7)መሀመድ ሼሁ 😎 አህመድ እንድሪስ 9) የሱፍ ሀሰን 10) አያሌው ዳውድ 11) ሙሳ ክብረት 12) መሀመድ ሙሳ 13) ሰይድ ሙሳ 14) አህመድ የሱፍ 15) አሊ ዳውድ 16) ኢሳ መሀመድ 17) ሰዋለህ መሀመድ 18) ኢብራሂም አሊ 19) የሱፍ አሊ 20) መሬም ሙሳ 21) አህመድ የሱፍ 22) ኢብራሂም አያሌው 23) ሱሌማን ሰዋለህ፣ 24) ማርዬ ሰዋለህ(ወንድማማቾች) 25) ሰዋለህ በላይ (አባት) 26) ከድር ጋሻው 27) ጋሻው ዳውድ 28) ጅብሪል የሱፍ_አሙሩ ላይ ከ6 ወር በፊት አባቱ በኦነግ ሸኔ የተገደለበት፣ 29) አህመድ የሱፍ(ወንድማማቾች) 30) አደም ዘውዱ 31) የኑስ ዳውድ 32) ይብሬ በቀለ፣ 33) ፋጢመሰ ሙሀመድ 34) እባቡ ገደፋው 35) ዳውድ በሽር 36) አዲሱ ሰዋለህ 37) ኡስማን ይመር 38) ዳውድ ገበየሁ 39) ሀሩን መሀመድ 40) ጂብሪል አህመድ 41) እርስቱ ኡስማን 42) መሀመድ አህመድ 43) ቃሲም ሙጭዬ 44) ኡስማን ሁሴን 45) ሁሴን አህመድ 46) ሀሰን እሸተ 47) አማን ሰይድ አባት 48) አብዲ አማን 49) ጦይብ አማን(የአብዲ እህት) 50) ዳውድ የሱፍ 51) ሀሚድ ሀሰን 52) ወርቅነሽ አህመድ 53) አሊማ ፈንታው 54) ሀዋ ሞላ 55) የሱፍ አብደላ 56) ኢብራሂም ከተማው 57) አዳዶ ሙሀመድ 58) ጀምበር ይብሬ 59) ጋሻው ይብሬ (ወንድማማቾች) 60) ወርቄ ታዬ (የእነ ጀምበርና ጋሻው እናት) 61) ፋጡማ ዳውድ 62) ታርቄ አህመድ 63) እንድሪስ ኑሩ 64) ኡስማን አበባው 65) መሀመድ ታርቄ 66) ነጋ አየነው 67) ሼህ ጀማል መሀመድ 68) መሀመድ ሲራጅ 69) እንድሪስ ይመር 70) ቃሲም መሀመድ 71) አህመድ እርገጤ 72) ሙህዬ አረጋ 73) አህመድ አደም 74) ጅብሪል መሀመድ 75) ያሲን መሀመድ 76) ዳውድ የኑስ 77) እንድሪስ አህመድ 78) ዳውድ አህመድ 79) አህመድ አስማረ (የዳውድ አባት) 80) ሰይድ የሻው 81) ሙሀመድ ሰይድ 82) ክንዱ ሀሰን 83) ኡስማን ሙሄ 84) አቶ አበበ ይህ ሁሉ አማራ ከቀዬውና ከአዝመራው ሲፈናቀል ምንም ያላለው የአሙሩ ወረዳ አስተዳደር አቶ በላይ መከኖ ቀበሌ ላይ በስጋት ለቀዋል የተባሉ የ5 ኦሮሞዎች አንዳች ንብረት እንዳይነካ በማለት ከሰሞኑ አቶ ጌጡ ለማ ለተባሉ የመከኖ ቀበሌ ሊቀመንበር ደብዳቤ መጻፉ ተሰምቷል። ደብዳቤው የእነዚህ ተፈናቃዮች አንዲት ንብረት ብትነካ የአካባቢው ህዝብና ሚሊሻዎች ተጠያቂ ናችሁ የሚል ይዘት እንዳለው የአሚማ ምንጮች ገልፀዋል። በተያያዘ መከኖ ቀበሌ ዳቢት በተባለ ጎጥ ያሉ 20 የሚሆኑ የአማራ ሚሊሻዎችን ኑ መሳሪያ አስመዝግቡና ጥይት ውሰዱ መባሉን በሁለት ምክንያት ሚሊሾች እንዳልወደዱት ተገልጧል። መንገድ ላይ ለማስገደልና ለማሰር ሊሆን ይችላል በማለት፣ ከምንም በላይ ግን አካባቢውን ክፍት በማድረግ አማራዎችን ለማስጨፍጨፍና ለማፈናቀል ታስቦ ነው በሚል ጥርጣሬ መሆኑ ታውቋል። ትዕዛዝ ሰጭ ናቸው የተባሉት የአሙሩ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኃይሌ “ካልመጣችሁ በመከላከያ ትመታላችሁ” በማለት በስልክ መዛታቸው ለአሚማ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply