You are currently viewing በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ በተለያዩ የመንግስት አካላት ጭምር የሚደገፈው አሸባሪውና ዘር አጥፊው የኦነግ ሸኔ ቡድን ተኩስ ከፍቶብን ውሏል ሲሉ ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ በተለያዩ የመንግስት አካላት ጭምር የሚደገፈው አሸባሪውና ዘር አጥፊው የኦነግ ሸኔ ቡድን ተኩስ ከፍቶብን ውሏል ሲሉ ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ በተለያዩ የመንግስት አካላት ጭምር የሚደገፈው አሸባሪውና ዘር አጥፊው የኦነግ ሸኔ ቡድን ተኩስ ከፍቶብን ውሏል ሲሉ ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኦሮሚያ በሚባለው ክልል አጉል ጥላቻ እና የሀሰት ትርክት ያነሆለላቸው ነገን የረሱ የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ አባላት ከብዙ የመንግስት አካላት ጋር በመመሳጠር በአማራ ላይ ያለምንም ሰብአዊ እርህራሄ በሌሊት፣ በአደባባይና በጠራራ ፀሀይ የተደራጀ የጅምላ ፍጅት መፈፀም መደበኛ ስራ ካደረጉት ቆይተዋል። ከሰው ተራ በወጣ አሰቃቂ በሆነ መልኩ በጅምላ በማንነት ለይቶ መግደል፣ በመኪና ላይ እያሉ መጨፍጨፍ፣ መድፈር፣ መንገድ ዘግቶ ማስራብ፣ ማቃጠል፣ መዝረፍ እና ማፈናቀል የሽብር ቡድኑና መሰል የመጠፋፋት አላማ ተጋሪዎቹ የተለመደ ተግባር ሆኗል። ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2014 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ከአቢ ደንጎሮ ወደ ሻምቡ ምልምል ሰልጣኞችን ይዘው ሲጓዙ ነበሩ በተባሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ አርቡ ሾጤ በተባለ አካባቢ ለሰዓታት የቆዬ ተኩስ ከፍተው መዋላቸውና የቆሰለም ስለመኖሩ ተሰምቷል። አርቡ ሾጤ ላይ መስከረም 10 ቀን 2014 መረጃ ከቢሮ ሾልኮ ይደርሰዋል የተባለው የሽብር ቡድኑ በከፈተው ተኩስ ሁለት የፌደራል ፖሊሶች መገደላቸውና ሁለት መቁሰላቸውን አሚማ መዘገቡ ይታወሳል። በተመሳሳይ በአቢ ደንጎሮ ወረዳ ጉለንቴ ቀበሌ በሼህ ጎጥ መስከረም 12 ቀን 2014 ከቀኑ 10 እስከ 12 ሰዓት ለ2 ሰዓት ያህል በዝርፊያ ላይ የተሰማራው ኦነግ ሸኔ ከብቶችን ከመዝረፉ ባሻገር በአማራ አርሶ አደሮች ላይ ተኩስ ከፍቶ ማምሸቱ ተገልጧል። የሽብር ቡድኑ ጥሩምባ እየነፉ እና ሆ እያሉ የሚንቀሳቀሱ ዘራፊ ጀሌዎችን አስተባብሮ ይዞ መምጣቱ ታውቋል። በጉለንቴ 1ኛ ደረጃ ት/ቤትን እንደ ምሽግ በመጠቀም ከተዋጉ በኋላ በኢዶክሳ በኩል መጥቷል የተባለውን አጋዥ የአማራ ሚሊሻን በመፍራት ምሽግና ማሰልጠኛ ወዳደረገው ዴቢስ ባለእግዚአብሄር ቤተ ክርስቲያን መሸሹ ተነግሯል። ቡድኑና ተባባሪዎቹ በቀላሉ ከ150 በላይ ከብቶችን ዘርፎ ወደ ዴቢስ መውሰዱን የጉለንቴ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከብቶቻቸውን ከተዘረፉት አማራዎች መካከልም:_ 1) ሙሳ ዳምጤ፣ 2) ኡመር ዳምጤ 3) ገደፍ ጌጡ፣ 4) ዋሲሁን መኮንን፣ 5) ፍስሃ ዋሲሁን፣ 6) ክንዱ ዋሲሁን፣ 7) ኡመር ክብረቱ ፣ 😎 አረጋ አባተ፣ 9) አህምዬ ክብረቱ 10) ጌታቸው ደርሶና 11) ጎበዜ አያሌ ይገኙበታል። የተጎዳ ሰው ስለመኖሩ እርግጠኛ አለመሆናቸውን የተናገሩት የጉለንቴ ነዋሪዎች ለኦነግ ሸኔ ያደሩ መሪ ናቸው የሚባሉት አቶ ብሪሳ ኃይሌ የሚመሩት የወረዳ መስረዳድርም ድረስልን ተብሎ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግለትም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ መቅረቱን ነው የገለፁት። በተያያዘ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ 7 ቀበሌዎችን በወረራ ጥቃት የተቆጣጠረው የአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እንቅስቃሴ በተለይም በጋሌሳ አካባቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ በመምጣቱ ለከፍተኛ ስጋት የዳረጋቸው ጉዳይ መሆኑ ተገልጧል። መንግስት መከላከያ ወይም የአማራ ልዩ ኃይልን በአካባቢው እንዲያሰማራ የጠየቁት ነዋሪዎች ጋሌሳ ላይ ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ ማዘን ትርጉም ስለማይኖረው እሄኔ እንድትተባበሩን፣ እንድትጮሁልን ስንል ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል። በድባጤ ወረዳ ጋሌሳ ላይ እንደሰፈሩ የተነገረላቸው ልዩ ኃይሎች አዛዥ ናቸው የተባሉት ሻለቃ በላይም እየደረሱልን አይደለም ሲሉ ወቅሰዋቸዋል። ከከተማ ውጭ በሽብር ቡድኑ የተገደሉ የንፁሃንን አስከሬን አንስቶ ለመቅበር እንኳ ወደ ገጠር አንወጣም በማለት እየተባበሩን አይደለም ሲሉ ሻለቃ በላይን ይወቅሳሉ። ከሰሞኑ በኦነግ ሸኔ ታግተው የተገደሉት የእነ አባ አሳፋው ማርዬን አስከሬን እንኳ ለማንሳት ባለመተባበራቸው በእጅጉ ማዘናቸው ተገልጧል፤ በብስጭት አስከሬን ለማንሳት ከሄዱትም አማራዎችም ሁለት መቁሰላቸውን አሚማ መዘገቡ አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply