You are currently viewing በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ 5 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በእኩይ አላማ ተጋሪዎቹ በግፍ ተገደሉ፤ የተጠናከረ ማንነት ተኮር ግድያን የሚያስቆም የመንግስት አካል አልተገኘም ተ…

በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ 5 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በእኩይ አላማ ተጋሪዎቹ በግፍ ተገደሉ፤ የተጠናከረ ማንነት ተኮር ግድያን የሚያስቆም የመንግስት አካል አልተገኘም ተ…

በሆሮ ጉድሩ ዞን አቢ ደንጎሮ ወረዳ 5 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በእኩይ አላማ ተጋሪዎቹ በግፍ ተገደሉ፤ የተጠናከረ ማንነት ተኮር ግድያን የሚያስቆም የመንግስት አካል አልተገኘም ተብሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂ ግድያ፣መፈናል፣እገታና ዝርፊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ስንቅ፣ ትጥቅና መረጃ በሚያቀብሉ በርካታ የመስተዳድር አካላት የተሞላው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ከኦነግ ጋር ያለው ትስስር የደም ብቻ ሳይሆን የአላማ ጭምር መሆኑን አስመስክሯል የሚሉት ብዙዎች ናቸው። ግድያ እና አፈናው ተጠናክሮ ቀጥሎ በአቢ ደንጎሮ ወረዳ ወንዶ በተባለ ቀበሌም ተፈጽሟል። ይኸውም በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የነበሩ 5 አማራዎች የካቲት 5 ቀን 2014 ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአሸባሪውና ወራሪው የኦነግ ሸኔ ገዳይ ቡድን በተከፈተባቸው ተኩስ 4ቱ ተገድለዋል። በወንዶ ቀበሌ በማንነታቸው የተነሳ በግፍ የተገደሉት አማራዎችም:_ 1) ሼህ የሱፍ መሀመድ_ የ4 ልጆች አባት፣ 2) አሚናት ጌታቸው_ የ4 ልጆች እናት፣ 3) ሀዋ ይመር (የአሚናት ጌታቸው የበኩር ልጅ) እንዲሁም፣ 4) አንሻ መሀመድ የተባለች የ12 ዓመት ልጅ ናቸው። ከቆሰሉት መካከልም ዘይንያ አህመድ የተባለች የ12 ዓመት ልጅ (ክፉኛ ተዳክማ በሆስፒታል የህክምና እገዛ እየተደረገላት ትገኛለች) እና አንድ ሚሊሻ እንደሚገኙበት አሚማ ከስፍራው ያጣራው መረጃ አመልክቷል። የ5 አባዎራ ከ100 በላይ ከብት እና ፍየል ተነድቷል፤ ዶሮ አልቀረም፤ ሁሉም ንብረት ተወስዷል። በግፍ የተገደሉ የ4 አማራዎች አስከሬንም በወንዶ ቀበሌ ካራ በር አካባቢ ተቀብሯል። አማራው ራሱን ከኦነግ ሸኔ ለመከላከል ያደረገውን ሙከራ በመቃወም የአቢ ደንጎሮ እና የጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ መስተዳድር በጋራ በውሸት ፋኖ ገብቷል እያሉ ከኦነግ ሸኔ በላይ እያሳደዱን ነውና ድረሱልን የሚል ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply