You are currently viewing በሆሮ ጉድሩ ዞን ኦዳቡልቅ/ሰቀላ ወረዳ በአማራ ላይ ሲደረግ የሰነበተውን ቅስቀሳ፣ ጥላቻና ፍረጃን ተከትሎ በጃርዴጋ እና አካባቢው ያሉ አማራዎችን ለማጥቃት አደገኛ እንቅስቃሴ መኖሩ ተገልጧል፤…

በሆሮ ጉድሩ ዞን ኦዳቡልቅ/ሰቀላ ወረዳ በአማራ ላይ ሲደረግ የሰነበተውን ቅስቀሳ፣ ጥላቻና ፍረጃን ተከትሎ በጃርዴጋ እና አካባቢው ያሉ አማራዎችን ለማጥቃት አደገኛ እንቅስቃሴ መኖሩ ተገልጧል፤…

በሆሮ ጉድሩ ዞን ኦዳቡልቅ/ሰቀላ ወረዳ በአማራ ላይ ሲደረግ የሰነበተውን ቅስቀሳ፣ ጥላቻና ፍረጃን ተከትሎ በጃርዴጋ እና አካባቢው ያሉ አማራዎችን ለማጥቃት አደገኛ እንቅስቃሴ መኖሩ ተገልጧል፤ አስቸኳይ ጥንቃቄ እንዲደረግም ጥሪ ቀርቧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ዞን ኦዳቡልቅ/ሆሮ ቡልቅ/ ሰቀላ ወረዳ በአማራ ላይ ከሰሞኑ በተለይም ህዳር 12/2015 በተደረገ ብዙ ሽህዎች የተሳተፉበት ሰልፍ እና ስብሰባ በአማራ ላይ ያተኮረ የጥላቻና ፍረጃ ቅስቀሳ እንደነበር ተገልጧል። በእለቱም ከፍተኛ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ የሸኔ አባላት፣ የአካባቢው ቄሮዎችና ብዙ ነዋሪዎች በሰልፉ እና በስብሰባው ተገኝተው ሀገር አልባ ተደርጎ በሸኔ እና በመንግስት አካላት ጭምር እየተጠቃ ያለው አማራን እንደ በዳይ በማድረግ በቁጣ የጥላቻ መፎክር ሲያሰሙ ውለው ነበር። አማራን ከአካባቢው እናስወጣለን ባሉት መሰረትም ህዳር 13/2015 በኦዳቡልቅ እንቅስቃሴ መኖሩን የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ነግረውናል። ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኦዳቡልቅ የኦሮሞ ተወላጆች ሰልፍ በማድረግ ከከተማው ለመውጣት እና ወደ አዋሳኙ ጃርዴጋ ለማቅናት እንቅስቃሴ ላይ ናቸው ተብሏል። በመሆኑም በጃርዴጋ እና አካባቢው ያሉ አማራዎችን ለማጥቃት አደገኛ እንቅስቃሴ መኖሩን በመገንዘብ አስቸኳይ ጥንቃቄ እንዲደረግ፣ የሚመለከተው የመንግስት አካልም በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወስድ የሚያሳስብ ጥሪ ቀርቧል። አሚማ የኦዳቡልቅ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪን አቶ ሽብሩን በስልክ አግኝቶ አነጋግሯል፤ የደረሰውን ቅሬታም አቅርቧል። አቶ ሽብሩ ለጊዜው በሻምቡ እንደሚገኙ በመግለጽ ህዳር 12/2015 በነበረ ሰልፍ ላይ ቅስቀሳ እንደነበረ መስማታቸውን አረጋግጠዋል። ይህን ተከትሎም በአማራዎች ላይ ጥቃት እንዳይፈጽሙ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ገልጸዋል። ሁኔታውን ከርቀት እየተከታተሉት እና መልዕክትም እያስተላለፉ መሆኑን በመግለጽ ችግር አይደርስም ይበሉ እንጅ ምንጮች እንደሚሉት እየተደረገ ያለው በስሜት እና በጥላቻ የተሞላ አካሄድ አስፈሪ እና በዘላቂነት ለማንም የማይበጅ ነው። በተያያዘ እየተናበበ እየተንቀሳቀሰ ነው የተባለው አሸባሪው ኦነግ ሸኔም በጃርዴጋ ሀቦ ቀበሌ በኩል ህዳር 13/2015 ተኩስ መክፈቱ ተሰምቷል። አሚማ ሁኔታውን እየተከታተለ ተጨማሪ መረጃዎችን የሚያጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply