በሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በገደለው ሰው ቤት ለእዝን በተቀመጡ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ስለማሳደዱ ወረዳ አስተዳዳሪው የደረሰኝ መረጃ የለም ሲሉ የቀበሌው አስተዳዳሪ ደ…

በሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በገደለው ሰው ቤት ለእዝን በተቀመጡ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ስለማሳደዱ ወረዳ አስተዳዳሪው የደረሰኝ መረጃ የለም ሲሉ የቀበሌው አስተዳዳሪ ደግሞ ከአቅሜ በላይ ነው በሚል ሪፖርት ስለማድረጋቸው ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኦነግ ሸኔ ጦር በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ሲደን ቀበሌ ለረዥም ጊዜ እየኖሩ 9 ልጆችን የወለዱት አቶ የኔአለም አየለን ጥቅምት 5 ለ6 ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ በቤታቸው ላይ ቦንብ በመወርወር እና ጥይት በመተኮስ መግደሉና ልጁንም በከፍተኛ ሁኔታ ማቁሰሉን መዘገባችን ይታወሳል። የአቶ የኔአለምን መገደል ተከትሎም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሀዘንተኞች በሲደን ቀበሌ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው የአቶ የኔአለምን ስርዓተ ቀብር መፈፀማቸው ይታወሳል። ይሁን እንጅ ስርዓተ ቀብሩን ፈፅመው የሟች ቤተሰቦችን እያፅናኑ ባሉ ሀዘንተኞች ላይ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈት ህዝቡን አሳደዋል። በወቅቱም መከላከያም ሆነ ሌላ የፀጥታ አካል የለም ሊደርስላቸው አለመቻሉን የጠቀሱት ነዋሪዎች በጫካ ሆነው የድረሱልን ጥሪ ማስተላለፋቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ማለዳ ላይ እንዴት ሆነው እንዳደሩ ያነጋገርናቸው አንድ አባት ጫካ ላይ እንዳደሩና ንጋት ላይም ከተበተኑ ልጆቻቸውና ባለቤታቸው ጋር ስለመገናኘታቸው ገልፀው ነገር ግን አካባቢያቸውን ኦነግ ሸኔ ስለከበበው ለመሄድ እንደማይችሉና በአቅራብ ወዳለ የገጠር ከተማ እያቀኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሌላኛው የሟች ወንድም ቄስ ድንቁ አየለ በበኩላቸው 11 የሚሆነ ቤተሰቦች ከጎጃም ተነስተው ለለቅሶ ወደ አሙሩ ወረዳ ሲደን ቀበሌ ከሄዱበት ተኩስ መከፈቱን ተከትሎ በጫካ ሲጓዙ ማደራቸውን አስታውቀው የደረሰላቸው የፀጥታ አካል አለመኖሩን ገልፀዋል። የሲደን በርከሊ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረጀ ቶሌራ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው ከገቡ 2 ሳምንት እንደሆናቸው በመግለፅ ከቀበሌው አቅም በላይ መሆናቸውን ለአሙሩ ወረዳ ሪፖርት አድርጌያለሁ ብለዋል። ዛሬ ያነጋገርናቸው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪም ግን የአቶ የኔአለም አየለ በኦነግ ሸኔ ጦር ከመገደሉ ውጭ በለቅሶ ቦታ ተኩስ ስለመክፈቱ የደረሰኝ መረጃ የለም ነው ያሉት። ይሁን እንጅ የአቶ የኔአለምን ግድያ የሚያጣራና የአካባቢውን የፀጥታ ሁኔታ የሚገመግም አንድ የፀጥታ መዋቅር መላካቸውን አስታውቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply