በሆሮ ጉድሮ ዞን አሙሩ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ 9 አማራዎች ማንነት ተኮር ግድያ ሲፈፅም፣ሲያፈናቅል እና ባንክ ሲዘርፍ በከረመው የኦነግ ሸኔ እና ቄሮ ቡድን ታገቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ…

በሆሮ ጉድሮ ዞን አሙሩ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ 9 አማራዎች ማንነት ተኮር ግድያ ሲፈፅም፣ሲያፈናቅል እና ባንክ ሲዘርፍ በከረመው የኦነግ ሸኔ እና ቄሮ ቡድን ታገቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ…

በሆሮ ጉድሮ ዞን አሙሩ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ 9 አማራዎች ማንነት ተኮር ግድያ ሲፈፅም፣ሲያፈናቅል እና ባንክ ሲዘርፍ በከረመው የኦነግ ሸኔ እና ቄሮ ቡድን ታገቱ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አገር በማፍረስ፣ ዘር በማጥፋት፣ ባንክ በመዝረፍ እና በሽብር ተግባር የተሰማሩት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከተባባሪ ቄሮዎች ጋር በመሆን አንዲት ሴትን ጨምሮ 9 ወጣቶችን ከሞተር በማስወረድ አግተው ኢረጲ ወደተባለ ስፍራ ስለመውሰዳቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል። እገታው የተፈፀመው በአሙሩ ወረዳ ሰሙ ኢላሙ ቀበሌ ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ ሲሆን ከታገቱት መካከልም ወጣት መሀመድ ይመር፣መሀሙዴ ሰይድ፣ጧሃዬ ሼህ አደምና ሁኔ ገርባው ይጠቀሳሉ። ከሳምንታት በፊት በሰሙ ኢላሞ ቀበሌ 2 አማራዎችን ስለመገደላቸውም ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከ3 ወራት በፊት አቶ አድማሱ የሱፍ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ሲገደሉ ድረሱልን ብለን ስንጠይቅ ያልደረሰው የአሙሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ረቢራ በማግስቱ የቀበሌ አስተዳዳሪው “ተከበናል፤ አማራ ሊገድለን ነው” በሚል በውሸት ሪፖርት ሲያደርግ በስፍራው ተገኝቶ አማራውን በመሰብሰብ ስም እየጠራ በማስነሳት ታደራጃላችሁ፣ እረፉ በማለት ካሸማቀቋቸው ሰዎች መካከል አቶ ሞላ አህመድ አንዱ ናቸው። ነዋሪዎች እንደሚሉት የወረዳ አስተዳዳሪው “አንተ ነህ አማራን እያነቃህ እና እያደራጀህ” በማለት ባስፈራሩት አቶ ሞላ አህመድም በሳምንቱ በኦነግ ሸኔዎች ከመኪና ላይ እንዲወርድ ተደርጎ ተገድሏል። ከአሙሩ ወረዳ ነዋሪ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ መከታተል ይችላሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply