በሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ የፈፀሙትን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ…

በሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ የፈፀሙትን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ…

በሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ የፈፀሙትን አሰቃቂ ግድያ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር ቆይታ ያደረጉት በሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የደርጌ ኮቲቻ ነዋሪዎች ናቸው። ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከባድ የቡድን መሳሪያዎችን ሁሉ ታጥቆ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማራው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ ሌሊት ላይ በፈፁሙት ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ 13 አማራዎች መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ኦነግ በጫቶ ጫካ እና በአካባቢው ተሰብስቦ ለተከታታይ 3 ቀናት እየመከረ ነው በሚል የተነገራቸውን መረጃ ውሸት ነው በማለት ያስጨፈጨፏቸው የጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይልም የቀብሩ እለት ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም መገኘታቸው ተሰምቷል። ቀብር ላይም ቦምብ ለማፈንዳት ሙከራ ያደረገው ኦነግ ሸኔ ትናንት ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም በአካባቢው አማራዎች፣ በሚሊሻዎችና በልዩ ሀይሎች ላይ ብሬን እና መትረጊዬስ ሲተኩስ ማርፈዱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ዘግይተው በስርዓተ ቀብር ወቅት ወደ አካባቢው ያቀኑት የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላትም ነገሩ ከአቅማችን በላይ ነው እናንተ መግባት ትችላላችሁ በማለት ሚሊሻዎችን ጥለው መሸሻቸውን የነገሩን ምንጫችን መንግስት ስለምን መከላከያ ሰራዊት አይልክም? ሲሉ ጠይቀዋል። መንግስት ሚሊሻውን አሰልጥኖ አስፈላጊውን የትጥቅ ግብአት ካሟላ እና ከኦነግ ጋር ሆነው የሚያስገድሉንን አመራሮች ፈትሾ ካስተካከለ እኛ እንበቃቸው ነበር ሲሉም ተናግረዋል። በመንግስት አካላት ድጋፍ ያለው፣ ትጥቅና ስንቅ እንደሚላክለት የተነገረለት፣ ከ20 በላይ ባንኮች የዘረፈውን ገንዘብ የአማራን ዘር ለማጥፋት፣ሌሎችን ብሄሮች ለመጨፍለቅ፣ለማፅዳት፣ለመስፋትና ለመንሰራፋት እየተጠቀመበት መሆኑ ግልፅ ስለመሆኑም ተነግሯል። ይህን በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ ላይ የተፈፀመውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተከትሎም እስከ ትናንት ብቻ ከ200 በላይ አማራዎች ቀያቸውንና ሀብት ንብረታቸውን ጥለው እየሸሹ መሆናቸው ተገልጧል። በለቅሶ ላይ ለስለላ የተገኘ አንድ ኦነግ እና ሌሎች ሁለት የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ መረጃዎች የተያዙ ቢሆንም በሽምግልና ሊለቋቸው እንደሚችሉ ነው የተጠቆመው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply