በሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ  ደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ አስተዳዳሪ በኦነግ ሸኔ ተገደሉ፤ ሁለት ልዩ ሀይሎችም መቁሰላቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ….

በሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ አስተዳዳሪ በኦነግ ሸኔ ተገደሉ፤ ሁለት ልዩ ሀይሎችም መቁሰላቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ….

በሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ አስተዳዳሪ በኦነግ ሸኔ ተገደሉ፤ ሁለት ልዩ ሀይሎችም መቁሰላቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሰሞኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና ተባባሪዎቻቸው በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ደርጌ ኮቲቻ በተባለ ቀበሌ 13 አማራዎችን በግፍ መግደላቸው ይታወሳል። በደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ ጫቶ በሚባል ጫካ የቡድን መሳሪያ ይዞ የመሸገው የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን በአማራ ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ መፈፀሙን ተከትሎ በርካቶች ተፈናቅለዋል። ዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ የአንድ የኦነግ ሸኔ አባልን ቤት ለመፈተሽ ባቀኑበት የደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ አስተዳዳሪ እና በልዩ ሀይል አባላት ላይ ተኩስ በመክፈት የቀበሌ አስተዳዳሪውን አቶ አሰበ ጌታን ሲገድሉ ሁለት ልዩ ሀይሎችን ማቁሰላቸው ተገልጧል። ምንጮች እንደገለፁት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ አስከሬን ለማንሳት አልተቻለም። ከልዩ ሀይሎች በተጨማሪም የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢው እንዲላክላቸው ነው ነዋሪዎች የጠየቁት። በደርጌ ኮቲቻ ቀበሌ ጫቶ በተባለ ጫካ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦነግ ሸኔ ኃይል እንዳለ ቢታወቅም እስካሁን አንድም እርምጃ አልተወሰደበትም

Source: Link to the Post

Leave a Reply