በሆቴሉ በደረሰው አደጋ ምክንያት ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አለፈ፡፡

በትላንትናው እለት በደረሰው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በሆቴሉ አልጋ ተከራይተው የነበሩ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው ማለፉ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

በትላንትናው እለት የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:08 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሁለት ቁጥር አዉቶቢስ ማዞሪያ አካባቢ አዲሱና ቤተሰቦቹ በተባለዉ ሆቴል ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ህይወታቸዉ ያለፈዉ ወጣቶች መሆናቸው የተናገሩት አቶ ንጋቱ ማሞ እድሜያቸዉ 28/30 ዓመት የተገመቱ ሲሆን በሆቴሉ አልጋ ተከራይተዉ ተኝተዉ የነበሩ ናቸዉ ብለዋል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሰባት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከሰላሳ ሁለት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋ ወደ ሌሎች የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርሰ መቆጣጠር ተችሏል።

አደጋዉ የደረሰበት ቦታ የአደጋ መቆጣጠሪያ ተሽከርካሪዎችን የማያስገባ በመሆኑ የአደጋ መቆጣጠር ስራውን አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበር ኮሚሽኑ አስታውቃል።

በሌላ በኩልም ትላንት በለ ሚኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ስምንት በአንድ ሬስቶራንት ላይ የጋዝ ሲሊንደር ፈንድቶ በተነሳ የእሳት አደጋ ሶስት ሰዎች ጉዳት ደርሷአል።

ህብረተሰቡ በተለይም የሆቴልና የንግድ ተቋማት ለእሳት አደጋ መከሰት የሚያጋልጡ አሰራሮችን በማስወገድ ቅድሚያ ለደህንነት እንዲሰጡ አቶ ንጋቱ እያሳሰቡ ማናቸዉም አደጋዎች ሲያጋጥሙ አደጋዉ ሳይባባስ በ939 የአደጋ ጥሪ መቀበያ ስልክ ቁጥር ፈጥነዉ እንዲያሳዉቁ መልክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply