በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የቁሊቲ ሰፈር ነዋሪዎች ቤታቸው ለልማት ይፈለጋል በሚል በእስካቫተር እንዲፈርስ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 7 ቀን…

በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የቁሊቲ ሰፈር ነዋሪዎች ቤታቸው ለልማት ይፈለጋል በሚል በእስካቫተር እንዲፈርስ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የወረዳ 14 አስተዳዳሪ በሰፈሩ በመምጣት “ፕሮጀክቱ” ከታጠረ ከ2010 በኋላ የተሰራ ቤት ነው የሚፈርሰው ሌላው አይነካም ብሏቸው እንደነበር የገለጹት በየካ አባዶ ለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የቁሊቲ ሰፈር ነዋሪዎች ናቸው። ከአሁን ቀደም በርካታ ቤቶችን በኃይል ለማፍረስ የተደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወም እስከ ከንቲባ ጽ/ቤት ድረስ ለአቤቱታ ቢመጡም የሚሰማቸው እንዳልተገኘ የሚያስታውሱት የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ይባስ ብሎ ብዙዎች ለእስር፣ ለድብደባ እና ለእንግልት ተዳርገው እንደነበር ገልጸዋል። “ጣራውን ብቻ አንሱት እና በውስጥ ሸራ ወጥራችሁ ኑሩበት፤ ከዛም እኛ እንደፈረሰ ሪፖርት እናደርጋለን” በማለት ካታለለ በኋላ እስካቫተር ልኮብናል ሲሉ አስተዳዳሪውን ወቅሰዋል። አሁን ላይ ከ2010 ጀምሮ የተገነባውን ነው የምናፈርሰው ይበሉ እንጅ ከፋፍለው ለማፍረስ እንደሆነ ይሰማናል፤ ለሌሎችም በቀጣይ ምንም ዋስትና የላቸውም ብለዋል ቅሬታ አቅራቢዎቹ። ከእለተ እሁድ ህዳር 4/2015 ጀምሮ በወረዳ 14 ቁሊት ሰፈር ብቻ 109 የሚሆኑ ቤቶችን በመለዬት እና ቀለም ከመቀባቱም በላይ አስተዳደሩ ለብቻ ሰብስቦ ቤታችሁ ስለሚፈርስ ቆርቆሮውን አንሱ ማለቱ ተወስቷል። ይህን ተከትሎ ህዳር 7/2015 ከንጋት ጀምሮ ሰፈሩ በፖሊስ ዙሪያውን ከተከበበ በኋላ ቤታችን በእስካቫተር እንዲፈርስ እየተደረገ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥረው ግረው ባገኙት ገንዘብ ገዝተው እና በከፍተኛ ወጭ ገንብተው ለብዙ ዓመት የነበሩበትን ቤት “ህገ ወጥ ነው፣ ለልማት ይፈለጋል” በሚል የማፍረስ ሂደቱንም እንደ ዜጋ በጣም አሳዛኝ እና ተስፋ አስቆራጭም ነው ብለውታል። ፎቶ_ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply