በለንደን ደርቢ አርሰናል ድል አድርጓል

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር አርሰናል ከቼልሲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ካይ ሀቨርትዝ 2x ፣ ቤን ዋይት 2x እና ሊያንድሮ ትሮሳርድ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቤልጂየማዊው የአርሰናል ተጨዋች ሊያንድሮ ትሮሳርድ በውድድር አመቱ አስረኛ የሊግ ግቡን ከመረብ አሳርፏል።

ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ ለአርሰናል በመጀመሪያ አመቱ አስራ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

አርሰናል በቀጣይም በሰሜን ለንደን ደርቢ ከቶተንሀም ጋር የሚጫወት ይሆናል።

በጋዲሳ መገርሳ
ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply