You are currently viewing በለገጣፎ ዳሌ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ከህዝብ ጋር በተጣላው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ፈርሶ አግኝተውታል። በለገጣፎ ዳሌ መጋቢት 19/2015…

በለገጣፎ ዳሌ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ከህዝብ ጋር በተጣላው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ፈርሶ አግኝተውታል። በለገጣፎ ዳሌ መጋቢት 19/2015…

በለገጣፎ ዳሌ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ከህዝብ ጋር በተጣላው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ ፈርሶ አግኝተውታል። በለገጣፎ ዳሌ መጋቢት 19/2015 የቤታቸውን መፍረስ የተመለከቱት ተማሪዎች የቤት እቃዎችን ተሸክመው ከሰፈራቸው ሲሰናበቱ ያሳያል። ከህዝብ ጋር ላይታረቅ የተጣላው እና ቅቡልነት ያጣው ከህወሓት መራሹ ስርዓት እብሪት፣ድንቁር እና ትዕቢት በነጻ ለመማር ያልፈቀደው፣ አገዛዝ የኖረ የህዝብ ጥላቻውን በሚያሳይ፣ አሳፋሪ እና አሳዛኝ በሆነ መልኩ አሁንም የዜጎችን ቤት በእስካቫተር እና በአፍራሽ ግብረ ኃይል መናዱን ያለ ሀፍረት ቀጥሎበታል! በአዲስ አበባ እና በአዲሱ የኦህዴድ አጠራር ሸገር ሲቲ ከእያቅጣጫው ያለ ቅንጣት የሰብአዊ እርህራሄ አብዛኞች የቀን ስራ ሰርተው፣ ለፍተው፣ጥረው ግረው፣ ውጭ ሀገር ተሰደው ያገኟትን ሀብት በማፍሰስ ገንብተው ለበርካታ ዓመታት የኖሩበት ቤታቸው በግፈኞች እየፈረሰባቸው “ድረሱልን!” የሚሉ መፍትሄ አልባ ድምጾችን መስማት እየተለመደ መጥቷል። በሱሉልታ፣በሰንዳፋ፣በቡራዩ፣በለገጣፎ ለገዳዲ፣ በገላን ሲዳማ አዋሽ፣ በጨሪ መድኃኒያለም፣ በኤርቱ ሞጆ፣ በኩራ ጅዳ አርባ አራት ማዞሪያ፣ በጀሞ ተራራ መድኃኒያለም፣ በፋኑኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ፣ በለሚ ኩራ፣ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 5 እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች የዜጎች ቤት የተፈጥሮ ማንነታቸው ጭምር እየታዬ ክፉኛ ወድሟል። በበርካቶች አካባቢ አሁንም መፍረሱ ተባብሶ ቀጥሏል። በፈረሱት የተለያዩ አካባቢዎች ተንጠንቶ ሰፊ ቁጥር ያላቸው አማራዎች ባሉበት አካባቢ የማፍረስ፣ የማፈናቀል እና የማሳደድ ዘረኛ ተግባር እየተፈጸመ ቢሆንም በርካታ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጭምር የጥቃቱ ሰለባ እየሆኑ ይገኛል። ፍትህ ለወገኖቻችን! ዜጎችን ከአዲስ አበባ ማፈናቀል ይቁም! ፎቶ_Keleb_Aster siyoum

Source: Link to the Post

Leave a Reply