በሊሙ ወረዳ 8 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ፣ በትህነግ እና በጉምዝ የሽፍታ ቡድን አባላት በግፍ ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 9 ቀን 2015 ዓ/ም አዲ…

በሊሙ ወረዳ 8 አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ፣ በትህነግ እና በጉምዝ የሽፍታ ቡድን አባላት በግፍ ተገደሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 9 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ መንደር 7 እና መንደር 8 አካባቢዎች የገቡ የኦነግ ሸኔ፣ የትሕነግ እና የጉምዝ የሽፍታ ቡድን አባላት በአማራዎች ላይ ግድያ እና ዝርፊያ መፈጸማቸው ተገልጧል። ህዳር 8/2015 በፈጸሙት ጥቃት በተለይም በመንደር 7፣ ስምንት አማራዎች መገደላቸውን የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ተናግረዋል። በሽብር ተግባር የተሰማሩ አካላት ጥቃቱን በፈጸሙበት ወቅት በአልሞት ባይ ተጋዳይነት በተሰጠ የአጸፋ ምላሽ አንድ አባላቸው የተገደለባቸው መሆኑ ተሰምቷል። በምስራቅ ወለጋ ዞን የሊሙ ወረዳ እና አካባቢው ከከማሼ ዞን ሚዥጋ ወረዳ የሚዋሰን ሲሆን በአካባቢው የኦነግ ሸኔ እና የትሕነግ የሽብር ቡድን አባላትን ጨምሮ የጉምዝ የሽፍታ ቡድንና ቤኒን የሚንቀሳቀሱበትና የሚያሰለጥኑበት መሆኑ ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply