You are currently viewing በሊቢያ በጎርፍ አደጋ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ 5 ሺህ ተሻገረ፡፡

በሊቢያ በጎርፍ አደጋ ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ 5 ሺህ ተሻገረ፡፡

ከትላንት በስትያ በአፍሪካዊቷ ሃገር ሊቢያ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ የበርካቶችን ህይወት ነጥቋል፡፡

የሰዎች አስክሬን በየቦታው ወድቆ ይገኛል” ብለዋል መቀመጫውን ምስራቃዊ ሊቢያ ያደረገው የመንግሥት ቃል አቀባይ ሚንስትር።

100ሺህ ነዋሪ ባላት ደርና ከተማ ውስጥ የነበሩ ሁለት ግድቦች እና አራት ድልድዮች ከተደረመሱ በኋላ ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በውሃ ተውጣለች።

የቀይ መስቀል ማኅበር በወደብ ከተማዋ ደርና እስካሁን ድረስ 10ሺህ ነዋሪ የገቡበት አለመታወቁ ሪፖርት ተደርጓል ብሏል።

እሁድ ዕለት የዘነበው ከፍተኛ ዝናብ ቤንጋዚ፣ ሶውሳ እና አል-ማርጅ ከተሞችን ጨምሮ በምስራቅ ሊቢያ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።

“እስካሁን የ1ሺህ ሰዎች አስክሬን ተነስቷል። የከተማዋ ሩብ ክፍል ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ብል ማጋነን አይሆንም።

በጣም ብዙ ብዙ ሕንጻዎች ፈርሰዋል” ብለዋል የአቪዬሽን ሚንስትሩ እና የአስቿኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባሉ ሂቼም ቻኪኦት።

በሊቢያ የቀይ መስቀል ኃላፊ የሆኑት ታሚር ራማዳን በጎርፍ አደጋው ምክንያት የሟቾች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply