በላሊበላ ከተማ የውሀ ፍሰትን ለመጨመር የሚያስችል የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ተከላ በመጪዉ አንድ ወር ይጠናቀቃል ተባለ::

የላሊበላ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ፅህፈት ቤት በከተማዋ የውሀ ፍሰትን ለመጨመር የሚያስችል የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ተከላ በመጪዉ አንድ ወር ይጠናቀቃል ብሏል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የፀሀይ ሀይል ማመንጫው ግንባታ የተጀመረው ታህሳስ ወር እንደሆነና ስራዉ በፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል ።

የፅህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ መለሰ አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የሶላር ፓናሉ ተነጥፎ ማለቁን እና ጠላቂ ፓንፕ እንዲሁም ሰርፌስ ፓንፖ እቃዎች እስኪመጡ እየተጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የጠላቂ ፓንፕና የሰርፌስ ፓንፕ ግዢ ቢፈፀምም እስካሁን ወደ ሃገር ውስጥ መግባት አለመቻላቸውንም ገልጸዋል፡፡
እነዚህ እቃዎች እጃችን ላይ ከደረሱ በአንድ ወር ውሰጥ ስራውን እናጠናቅቃለንም ብለዋል፡፡

ስራው ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በተለያዩ ምክንያት የመብራት አቅርቦት ቢቆራረጥም ያለመቸገር ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለህብረተሰቡ ለማድረስ ትልቅ ግብአት እንደሚሆን አቶ መለሰ ተናግረዋል፡፡

በሀመረ ፍሬዉ
ሚያዝያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply