በላፍቶ ክፍለ-ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ የተገነባው አዲሱ የገበያ ማዕከል ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ትላንት በቀን 16/04/2013 በሰጡት መግለጫ ጃልሜዳ የሚገኘው ጊዜያዊ የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ የገበያ ስፍራ የከተማው አስተዳደር ባዘጋጀው የገበያ ማዕከል እንዲዘዋወሩ በተወሰነው መሰረት የዕጣ ማውጣት እና ውል የመዋዋል ስርዓቱ ተጠናቋል፡፡

ከዛሬ ታህሳስ 17/04/2013 ጀምሮ ጃልሜዳ የነበረው የአትክልት ተራ በአዲስ አበባ የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ገበያ ማዕከል ስራ የጀመረ መሆኑን ቢሮው ለአሀዱ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

**************************************************************************

ዘጋቢ ፡ ሸምሲያ አወል

ቀን 17/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply