በሌለ ስልጣን ፡ ባልተጨበጠ ተስፋ የመናጨት ባህል =========== ሸንቁጥ አየለ ====== በሌለ ስልጣን ፡ ባልተጨበጠ ተስፋ የመሻኮት ባህል ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ከቅንጅት…

በሌለ ስልጣን ፡ ባልተጨበጠ ተስፋ የመናጨት ባህል =========== ሸንቁጥ አየለ ====== በሌለ ስልጣን ፡ ባልተጨበጠ ተስፋ የመሻኮት ባህል ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ከቅንጅት አመራሮች መማር ድንቅ ነበር።የሚማር ቢኖር ኖሮ። ቅንጅት ገና በዉህደት ሂደት ዉስጥ እያለ ልደቱን ገፍተን ብርቱካንን ወደፊት እናምጣት በሚል ትብታብ ዉስጥ ወድቆ ነበር።ልደቱ አያሌዉ ከአስር አመት በላይ ሲታገል ቆይቶ ወራት ያልታገለችዉን ብርቱካንን የልደቱ ንግስት ትሁን ብለዉ ሿሚና ሻሪ የሆኑት ደግሞ በወቅቱ አመት እንኳን ያልታገሉት እነ ብርሃኑ ነበሩ። የሚያስደንቀዉ ደግሞ ከአአ ዩኒቨርስቲ 40 ፕሮፌሰሮች አማራ ናችሁ ወይም ኢትዮጵያዊነትን ታከራላችሁ ተብለዉ ሲባረሩ በእነዚህ ሰዎች መባረር ተስማምቶ የወያኔን ዉሳኔ ደግፎ የአአዩ የክብር እንግዳ የሆነዉ የወያኔ የአደባባይ ወዳጂ ብርሃኑ ነጋ ልደቱን ለማጥላላት የተጠቀመበት ታክቲክ ልደቱ የወያኔ የጓዳ ሰላይ ነዉ የሚል ነበር።”መስረቅስ እየሳቁ በአደባባይ” አሉ የሌብነት ጥበብን ሰባኪዉ ሽማግሌ። እናም ህዝብ የአደባባዩን የወያኔ ወዳጅ ትቶ በጓዳ የወያኔን ወዳጅ ሲያስሥ እነ ብሬም ብርቱካንን ንግስት ሊያደርጉ ሲጋጋጡ፡ ልደቱም የቅንጅት አመራሮች በቋጠሩበት ደባ የበቀል ስሜት ዉስጥ ገብቶ ሲንፈራገጥ ኢትዮጵያ ላይ ልትወጣ የነበረች ጸሀይ መልሳ ጠለቀች። አመራሮቹ ወደ እስር ቤት ሲጣሉም በእስር ቤት ሳይቀር ብርሃኑ ነጋ ቅንጅት ዉስጥ አማራ በዝቷል ፡ ትግላችን አማራን መልሰን ወደ ስልጣን ልንመልስ አይደለም ሲል የሰማዉ ማሙሸት አማረ (በወቅቱ የቅንጅት ወጣት አመራር ቢሆንም) ከብርሃኑ ነጋ ጋር ዱላ ቀረሽ ክርክር ዉስጥ ገብቶ እንደነበረ በወቅቱ በስር ቤት ያሉ ይመሰክራሉ። የብርሃኑ ስጋት የነበረዉም የሌለ ስልጣን ፡ ያልተጨበጠ ተስፋ ነበረ። የደባ ጥቅል ዉጤቱ ግን ግም 7 ተቋቁሙ 10 አመት እሮጦም እንኳን ዞሮ ሲባዛ በዜሮ ሆኖ ብርሃኑ ነጋም የህዝብ አንገት አሳራጅ ሆኖ ይሄዉ እራሱም በባርነት ይማቅቃል። አቢይ አስገድዶ ብርሃኑን ካልሲ አጣቢ አድርጎታል። አሁን ያዉ የፖለቲካ ልምድ አለቅ ብሎ ይመስላል ፋኖዎች እንዳይግባቡ በሌለ ስልጣል ፡ ባልተጨበጠ ተስፋ ፋኖዎችን ጠቅልዬ በቁጥጥሬ ካላደረግሁ ወይም ካልጠፉልኝ የሚል ብሂል እንደ ጉድ እየተገመደ እና እየተፈተለ ነዉ። በአማራ ህዝብ ስም በቀኝና በግራ ቆሞ ሲምል እና ሲገዘት እየዋለ ዞር ብሎ ግን በአማራነት የተደራጀዉን ወንድሙን በእኔ ስር ካልመጣህ ብሎ ሲያሳድድ የሚዉለዉ ብዛቱ ለጉድ ነዉ። አንተ የአማራ ብሄረተኛ ነኝ ብለህ የአማራ ስም ለፖለቲካ መነገጃ ብትጠራ ብርሃኑ ነጋብ የኢትዮጵያ ብሄረተኛ ነኝ ብለህ የኢትዮጵያን ስም ብትጠራ ያዉ ሁለትህም መርገምት ነጋዴ ብሎም ደም ነጋዴ ነህ። የታጠቀዉን እና የተደራጀዉን ፋኖ ሁሉ በአንድ አግባብቶ የአቢይ አህመድን መንግስት በጋራ ደምስሦ የኢትዮጵያን ስነመንግስት ከተቆጣጠሩ ብኋላ ስለ ስልጣን ክፍፍል መደራደር መከራራከር መወያዬት ሲቻል የሌለ ስልጣን ፡ ያልተጨበጠ ተስፋ እያሰሉ መኮራረፍ እና መናጨት የዝንጆሮ ህሳቤ ነዉ። መሬ ብቻዉን ገጥሞ አንድ ወር ሙሉ በመንግስት ደረጃ የተደራጀዉን የአቢይ መከላከያ ሰራዊት እየተዋጋዉ ሸዋሮቢት ለጥ ብሎ በጀርባዉ ተኝቷል። ተጉለት፡ ደራ ፥ ጅሩ ፡ መንዝ እንዲሁም ሌላዉ የሸዋ ወረዳ በምን አገባኝ ቆሞ ያስተዉላል። የጎጃም የጎንደር እና የወሎዉማ እጅግ ሩቅ ነዉ። ከዚህ በፊት ከጉራፋርዳ ግማሽ ሚሊዮን አማሮች ሲባረሩ አንድ ተመሳሳይ ጉድ ተምሬ ነበር።የማይጠቅመኝ ትምህርት ሆኖ ቀርቷል። ብጽፈዉም ያነበበና የተማረበት የለም።ኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ የሚገቡ ሰዎች በነገዳቸዉ የተነሳ ሳይሆን በሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል የተነሳ ፍርዳቸዉ እንደ ዝንጆሮ ፍርድ ነዉ። ከቀደመዉ ስህተት ከመማር ይልቅ ጭብጥ እሸት እስኪቀነጭብ አይኑን አፍጦ ህሊናዉን ጋርዶ ጭራዉን ቆልፎ የሚሮጥ ነዉ።በዚህ የቁስ ሰቀቀን በወዲያ የእዉቀት ባዶነት የሚያንገዳግደዉ ፖለቲከኛ ይበዛል።ለመቧደን ይፈጥናል።ለመበላላትም ይሄዉ ነዉ። እናም በጉራ ፋርዳ የሚኖሩ አማሮች አሰፋፈራቸዉ ከጎንደር ከጎጃም ከወሎ ከሸዋ ደግሞ ከመንዝ ከመሬ እያሉ ለካ እርስ በርስ ይተዋወቁ ኖሯል። እናም ወያኔ በሽፈራዉ ሽጉጤ በኩል ቤታቸዉን ያስፈርስባቸዉ የነበረዉ እየነጣጠለ ተራ በተራ ነበር።ይሄን ታሪክ ከተረዳሁ ብሁላ “ያንድኛችሁ አካባቢ ሲፈርስ ለምን በጋራ ሆ ብላችሁ አልተቃወማችሁም ? ካስፈለገስ ለምን በጋራ አፍራሾቹን አትገጥሟቸዉም ?” ብዬ ብጥይቅ ያገኘሁት መልስ ልክ አሁን ያለዉን ሁኔታ ይመስላል። እያንዳንዱ ሌላዉ ሲጠቃ ጨርቁን አፍንጫዉ ላይ ጣል አድርጎ ቆሞ ያስተዉላል። ====== “ጽሁፍ አታቁም ! ዝም ብለህ ጻፍ” አሉ ፕሮፌሰር ሀብተጊዮርጊስ። “አትሰልች ዝም ብለህ ጻፍ ።” ጽሁፍ እንዳላቆም ሲያበረታቱኝ መሆኑ ነዉ። እኔም ዝም ብዬ እጽፋለሁ።የእኔ ጽሁፍ ሳይሆን ኢትዮጵያን የሚያድናት መድሃኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በመንፈስ በደንብ አዉቃለሁ።የህሊና የአእምሮ ብሎም የልብ እዳ ግን አለብኝና የዝንጀሮ ፍርድ እሴት ሰፈነ ተብሎ መጻፍ አይቆምም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply