በሌላ ዜና እስራኤል በስምምነቱ መሰረት  ይዛቸው ከነበሩት 39 ፍልስጤማውያንን ለቃለች።ቀይ መስቀል እስካሁን 24 ታጋቹች መለቃቀቸውን አሳውቋል ።ቀደም ብሎ 12 የታይላንድ ዜጎች ከሐማስ እገ…

በሌላ ዜና

እስራኤል በስምምነቱ መሰረት  ይዛቸው ከነበሩት 39 ፍልስጤማውያንን ለቃለች።

ቀይ መስቀል እስካሁን 24 ታጋቹች መለቃቀቸውን አሳውቋል ።

ቀደም ብሎ 12 የታይላንድ ዜጎች ከሐማስ እገታ ነጻ መውጣታቸውን የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቀው ነበር ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኤምባሲ ኃላፊዎች “ታጋቾቹን ሊወስዱ እያመሩ ነው” ያሉ ሲሆን፣ ታጋቾቹን ከየት እና መቼ እንደሚቀበሉ ግን ያሉት ነገር የለም።

ቀደም ሲል ግብፅ ከከፍተኛ ጥረት በኋላ 12 የታይላንድ ዜጎች እንዲለቀቁ አድርጊያለሁ ብላ ነበር።

የታይላንድ ዜጎች መለቀቅን በተመለከተ እስካሁን በሐማስ በኩል የተባለ ነገር የለም።

የታይላንድ ዜጎች መለቀቅ የተሰማው እስራኤል ሴቶች እና ሕጻናት የሆኑ 13 ታጋቾችን በቀይ መስቀል በኩል ከሐማስ እገታ ነጻ ይወጣሉ ብላ እየተጠባበቀች ባለበት ሰዓት ነው።

አደራዳሪዋ ኳታር በበኩሏ እስካሁን 13 እስራኤላውያን : 10 የታይላንድ  ዜጎች  እንዲሁም 1 ፌሊፒማዊ ተለቀዋል።

ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ 230 ያላሱ ሰዎችን አግቶ ወደ ጋዛ ሰርጥ መውሰዱ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply