በልማት ላይ ያለ መንግስት የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር ይቸገራል… ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይህንን የተናገሩት፤
በመካሄድ ላይ ባለው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

በሁሉም አለም የዋጋ ግሽበት እንዳለ ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኑሮ ውድነቱ በእኛ ብቻ እንዳልሆነ ህዝቡ መገንዘብ አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል።

የዋጋ ግሽበቱን ለመፍታት ምን መደረግ አለበት በማለት ትላልቅ ምሁራንን እንዳማከሩ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤

መንግስታቸው ፈጣን ልማት ተኮር ላይ በመሆኑ ያለው አማራጭ ልማቱን መተው እንደሆነ ከምሁራኑ ምላሽ እንዳገኙ አስታውሰዋል።

የኮሪደር ልማት መዝናኛ ቦታዎች እና መሰል የመንገድ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ እንደሆነ ያነሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ነገር ግን ልማትን መተው ለኑሮ ውድነቱ መፍትሄ እንደማይሆን አስቀምጠዋል።

የዋጋ ግሽበቱን በመቀነስ ከልማቱ ጋር እኩል አብሮ እንዲሄድ ማስቻል ዋነኛ መፍትሄ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ በቡና በማር አና በስንዴ ምርት በአንደኝነት ከአፍሪካ እየመራች እንደሆነ ገልፀ፤
የቅዳሜ እና እሁድ ገብያ ቁጥራቸውን በመጨመር በኑሮ ውድነቱ ለሚፈተነው ማህበረሰብ መድረስ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በለዓለም አሰፋ
ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply