በሐገሪቱ ምርጫ የተሳተፈውና በቁም እስር ላይ የሚገኘውን ቦቢ ዋይን ለመጎብኘት የሄዱት በኡጋንዳ በሐገሯ የአሜሪካ አምባሳደር በሐገሪቱ ባለ ስልጣናት ተከለከሉ፡፡

ሳምንት ሐሙስ በሐገሪቱ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ቅዳሜ እለት ይፋ ሲሆን ያለፉትን 35 ዓመታት ሐገሪቱን የመሩት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ለ6ኛ ጊዜ ምርጫውን ማሸነፋቸው ተበስሯል፡፡

በምርጫው ላይ ብርቱ ተፎካካሪ የነበረውና በመድረክ ስሙ ቦቢ ዋይን ተብሎ የሚጠራው እጩ ድምጹን ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በቁም እስር ላይ ነው የሚገኘው፡፡የባለፈው ሳምንት ምርጫን አሜሪካ ለመቀልበስ ፈልጋለች ስትል ኡጋንዳ ከሳለች፡፡ ሁለቱ ሐገራት በእንደዚህ ዓይነት መካረር ውስጥ ሆነው ነው በኡጋንዳ የአሜሪካ አምበሳደር ናታሊ ኢ ብራወን በቁም እስር ላይ የሚገኘውን ቦቢ ዋይንን ለመጎብኘት ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ የሆነባቸው፡፡

ቦቢ ዋይን በሐገሪቱ ያለውን ሙስና እና መድልኦ በዘፈኖቹ በማጋለጡ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡ አምባሳደሩ ዋይን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ደህንነቱና የጤናውን ሁኔታ ለመመልከት ነበር ለመጎብኘት የጠየቁት ብሏል ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ፡፡

የሐገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በፈረንጆቹ ከ1986 ጀምሮ በስልጣን ላይ የሚገኙት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በ58 ነጥብ 6 ድምጽ ማሸነፋቸውን አሳውቋል፡፡ 35 በመቶ ድምጽ አግኝቶ ሁለተኛ መሆኑ የተነገረው ቦቢ ዋይን ምርጫው በ76 ዓመቱ ሙሴቬኒ መጭበርበሩን በመጠቆም ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

*****************************************************************************

ቀን 12/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

ምስል፡- የአሐዱ ሎጎ

The post በሐገሪቱ ምርጫ የተሳተፈውና በቁም እስር ላይ የሚገኘውን ቦቢ ዋይን ለመጎብኘት የሄዱት በኡጋንዳ በሐገሯ የአሜሪካ አምባሳደር በሐገሪቱ ባለ ስልጣናት ተከለከሉ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply