በሑመራ ማረሚያ ቤት ከለውጡ ጀምሮ በሽብር ወንጀል የተፈረደባቸው የአ/ግንቦት( 7 ) አባላት እንዳሉ የትግል ጓዶቻቸው ገለፁ። አሻራ ሚዲያ ህዳር 1/3/2013 ዓ.ም ባህርዳ…

በሑመራ ማረሚያ ቤት ከለውጡ ጀምሮ በሽብር ወንጀል የተፈረደባቸው የአ/ግንቦት( 7 ) አባላት እንዳሉ የትግል ጓዶቻቸው ገለፁ። አሻራ ሚዲያ ህዳር 1/3/2013 ዓ.ም ባህርዳር በሽብርተኝነት ወንጀል የተፈረደባቸው የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች የነበሩ በሁመራ ማረሚያ ቤት የ24አመት ፍርደኞች ጠያቂ ያጡ ታጋዮች በግዳጅ የላካቸው ድርጅት ፓርቲ ታጋዮቹ የት እንዳሉ እንኳን አያውቅም ድርጅቱም ኢዜማ የተባለ ፓርቲ መስርቶ የእራሱን ስልጣን መጨበጫ መንገድ እያመቻቸ ታጋዮቹ ግን እስካሁን ተበታትነው ይገኛሉ ብለዋል የትግል አጋሮቹ። ከዚህ በፊት በነበረው ትግል ከኤርትራ በረሃ ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት የሕወሓትን ጦር ጋር በመግጠም የሕወሓትን መንግስት ከ4ኪሎ ቤተመንግሥት ወደ መቀሌ እንዲባረር በማድረግ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ታጋዮች አሁንም በስቃይ ላይ ናቸውም ብለዋል ። ሕወሓት ለ28 አመታት በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ የፈለገውን ያድርግ ነበር የሕወሓትን አገዛዝ ለመፋለም ብዙ የአማራ ወጣቶች ወደ ኤርትራ በረሃ በመሄድ የትጥቅ ትግሉን ይቀላቀሉ ነበር ያሉት የቀድሞው የአ/ግ(7) ታጋይ በወቅቱ የአማራ ወጣቶች የሚቀላቀሉት ድርጅት አርበኞች ግንባር ፣ አዴሃን ፣ ደሜሂት ግንቦት 7 በኋላ ግን አርበኞች ግንቦት 7 የሁሉም ኢትዮጵያዊ መዳረሻ ነበር ብለዋል ። አርበኞች ግንቦት 7 አብዛኞቹ በሚባል ደረጃ የአማራ ተወላጆች ወጣቶች የነበሩበት ድርጅት የነበረ ሲሆን አመራሩ በታጋዮች ላይ ትልቅ ቁማር ቆምሯልምተሰርቷል ብለዋል ። ከኤርትራ በረሃብ ብዙ ታጋዮች በግዳጅ ይላኩ ነበር በግዳጅ ወቅትም ብዙ ጀግኖች መሰዋት ሁነው ያሉ ሲሆን ከጦርነቱ የተረፉትም ወደ ቃሊቲ ቂሊንጦ በተለያዩ ማጎሪያ ቤቶች ይወሰዳሉ ። ከለውጥ በኋላ በፌዴራል ማረሚያ ቤት የታሰሩት ተፈተዋል ብለዋል። እስካሁን ሰአት ድረስ በስር ቤት የሚገኙት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች አሁንም በሁመራ ማረሚያ ቤት የ24 አመት ፍርድ ተፈርዶባቸው በስቃይ ላይ ያሉት ታጋዮች እንዳሉም ጓዶቻቸው ለአሻራ ሚዲያ ገልፀዋል ። እነዚህ ታጋዮች በ2009 ተልእኮ በመያዝ በወልቃይት አካባቢ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንዳሉ የሕወሓት ድህነት እና ጦር ባደረጉት ክትትል ከእጃቸው ላይ ወድቀዋል ። በኋላም አሸባሪዎች ናቸው በሚል ሁሉም ታጋዮች የ24አመት ፍርድ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት እንዳሉ ከ9ወር በፊት ለሚመለከተው ሁሉ አመልኩተን ነበር ብለዋል። ነገር ግን እስካሁን ደርስ በስቃይ ላይ ናቸው ተብሏል። አሁንም በሑመራ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙ የቀድሞው አርበኞች ግንቦት (7) ታጋዮች በቁጥር ስድስት(6)እንደሆኑ የገለፁት የትግል ጓዶቻቸው በአሁኑ ሰዓት ከሐዲው ህውሓትን ለመደምሰስ በግዳጅ ላይ ያለው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣የአማራ ልዩሀይል እና ፍኖ በሑመራ ማረሚያ ቤት በእስር እየተሰቃዩ ያሉ ታጋይ ጓዶቻችንን እንዲደሱላቸው ሲሉ የትግል ጓዶቻቸው ጥሪ አቅርበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply