በሕወሓት ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ በምስራቅ ሐረርጌ ተካሄደ

በሕወሓት ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ በምስራቅ ሐረርጌ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት በከሀዲው የሕወሓት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሐረማያ ከተማ ተካሄደ፡፡

ሰልፈኞቹ “ከሀዲው የሕወሓት ቡድንና ኦነግ ሸኔ ጠላቶቻችን ናቸው”፣ “ሀገራዊ የለውጥ ጉዟችን በጁንታውና በከሀዲው ሕወሓት የሞት ተላላኪ ቅጥረኞች አይደናቀፍም”፣ “ስግብግቡ የሕወሓት ጁንታ የፈፀመውን የሀገር ክህደት ወንጀል እናወግዛለን” የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ በከተማው ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ተዘዋውረዋል።

የሉዓላዊነታችን ጋሻና መከታ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊት በእውቀት፣ በሀብት እና በጉልበታችን እስከ መጨረሻው እንደግፋለን ማለታቸውንም ኢቢሲ ዘግቧል።

The post በሕወሓት ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ በምስራቅ ሐረርጌ ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply