በሕወኃት ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ

በሕወኃት ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስግብግቡ ጁንታ የሕወኃት ኃይል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ በስኬት መጠናቀቁን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢቢሲ በሰጡት መግለጫ የአየር ኃይል በወሰደው እርምጃ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ማውደም መቻሉን ገልፀዋል።

ሮኬቶቹ እስከ 300 ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችሉ በመሆናቸው እና በወንጀለኛው ቡድን ሮኬቶቹን የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቐለ እና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሣሪያ ማስቀመጫ ላይ የአየር ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ መደረጉ ተገልጿል።

The post በሕወኃት ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply