በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ አረብ ሊግ ያለውን የተሳሳተ አቋም ለማስተካካል እንደምትሰራ አልጄሪያ አስታወቀችበአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የውጭ ጉዳይ ሚ…

በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ አረብ ሊግ ያለውን የተሳሳተ አቋም ለማስተካካል እንደምትሰራ አልጄሪያ አስታወቀች

በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የተገኙት የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ራማታኒ ናማምራ ሀገራቸው ቀጣዩ የአረብ ሊግ ሊቀመንበርነቱን ቦታ ስለምትይዝ ፣ የአረብ ሊግ አባል ሀገራት በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ያላቸውን የተሳሳተ አቋም ለማስተካካል እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህንን ያሉት እየተካሄደ ባለው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ከምክትል ጠቅላይ ሚንስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ላይ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃልአቀባይ ዛሬ ከቀትር በፊት በሰጡት መግለጫ ላይ ነው፡፡

ከበፊትም ጀምሮ ከአልጄሪያ ጋር መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳለን ያነሱት ቃል አቀባዩ በህዳሴው ግድብ ላያ የሊጉ አባል አገራት ያላቸውን የተሳሳተ አቋም ለማስተካካል የበኩላቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በውይይት እንዲፈታ አልጄሪያ እንደምትደግፍም ናማምራ አክለው መግለጻቸው ታውቋል።

ራማታኒ ናማምራ በአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር በመሆን መስራታቸው ይታወሳል፡፡

በዳዊት አስታጥቄ
ጥቅምት 05 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply