በሕገወጡ ቡድን አስተባባሪነት በሁለት ዓመታት 113 ግጭቶች መቀስቀሳቸው ተገለጸ፡፡                    አሻራ ሚዲያ…

በሕገወጡ ቡድን አስተባባሪነት በሁለት ዓመታት 113 ግጭቶች መቀስቀሳቸው ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ…

በሕገወጡ ቡድን አስተባባሪነት በሁለት ዓመታት 113 ግጭቶች መቀስቀሳቸው ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-21/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ዋና ዋና የሚባሉና የበርካታ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፉ፣ ንብረት ያወደሙ እና የመንግሥትን ትኩረት የሳቡ 113 ግጭቶች ተከስተው እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች ብሔር እና ሐይማኖት ተኮር ግጭቶች እንዲነሱ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል፤ ግጭቶች ተነስተውም ጉዳት አስከትለዋል፡፡ በሁለት ዓመታቱ በእያንዳንዱ ሳምንት የጦርነት ድግስ የነበረበት መሆኑን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥት ተግባርም ልቅሶና ቀብር እንዲሆን ተደርጓል ብለዋል፡፡ የለውጡ ዋንኛ ጠላት (ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን) መንግሥት ፊቱን ወደ ልማት እንዳያዞር ያደራጃቸውን የውስጥ ኃይል በመጠቀም የሽብር ሥራዎችን ሲያከናውን እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡ የሕወሓት የጥፋት ቡድን መሪዎች በየቦታው የሚነሳውን ግጭት በሀሳብና በሎጂስቲክስ መምራታቸው ሳያንስ ትግራይ ክልል ብቻ አስተማማኝ ሠላም መኖሩን እንደ ጀብዱ ቆጥረው ማዕከላዊ መንግሥቱን አቅም አልባ አስመስለው ሲያወሩ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ በትግራይ ሰላም እንዲደፈርስ የሚሠራ ሌላ ኃይል አለመኖሩ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የግጭቶች ሁሉ ጠንሳሽ ስልጣናቸውን የተቀሙት የሕወሓት ቡድን አባላት መሆናቸው ትግራይ ክልልን የተለየ አድርጎታል፡፡ በተለይ በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ብዙ ጥፋት እንዲደርስና ባለስልጣንም ጭምር እንዲጎዱ ታሳቢ ያደረገ እንደነበር አንስተዋል፡፡ በአማራና በኦሮሞ መካከል ጦርነት እንዲነሳ መታሰቡንም አንስተዋል፡፡ ሀጫሉን እንደ ዋንኛ ጠላት ያዩት የነበሩ አካት የኦሮሞ ታጋይ ተገደለ ብለው ሲያራግቡ መታየታቸው በሀገሪቱ ለተከሰቱት ግጭቶች ሁሉ ጠንሳሽ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ ግጭቶች እንዲቀሰቀሱ የነበረው አሠራር በቀላል የሚታይ ሳይሆን በገንዘብ የተደገፈ፣ በስልጠና እና ሥምሪት የሚመራ እንዲሁም የበለጠ ችግር እንዲፈጠር በሚዲያ ጭምር የሚናፈስ እንነበርም አስታውሰዋል፡፡ በግጭቶቹ የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ የንብረት ውድመት መድረሱንና በርካቶች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕዝብ እርስ በእርሱ በጥርጣሬ እንዲተያይ ከማድረግ የዘለለ ባቀዱት መልኩ ውጤት እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply