You are currently viewing በመላው ዐለም የምንገኝ የዐማራ ማኅበራት የሚከተሉትን የጋራ አቋም መግለጫ ዛሬ ታኅሣሣ ፲ ፭/፳ ፻ ፲ ፭ አውጥተናል። ፩. አብይ አህመድ በሰኔ ፲ ፬ ቀን ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ…

በመላው ዐለም የምንገኝ የዐማራ ማኅበራት የሚከተሉትን የጋራ አቋም መግለጫ ዛሬ ታኅሣሣ ፲ ፭/፳ ፻ ፲ ፭ አውጥተናል። ፩. አብይ አህመድ በሰኔ ፲ ፬ ቀን ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ…

በመላው ዐለም የምንገኝ የዐማራ ማኅበራት የሚከተሉትን የጋራ አቋም መግለጫ ዛሬ ታኅሣሣ ፲ ፭/፳ ፻ ፲ ፭ አውጥተናል። ፩. አብይ አህመድ በሰኔ ፲ ፬ ቀን ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ኦሮሚያ ክልል በሚሉት ውስጥ ነፃ ውድድር ሳይኖር ራሱን አሸናፊ አስመስሎ ለማቅረብ መሞከሩ “ሕገ ወጥ” ነውና አብይ ኢትዮጵያን ወክሎ ከየትኛውም ቡድን ጋር እያደረገ ያለው ውይይት በተለይ ደግሞ ዐማራ ከ፲ ፱ ፰ ፫ የሎንደን የሰላም ውይይት ጀምሮ የራሱ እውነተኛ ወኪሎች ባልተሳተፉበት እየተደረገ ያለ ማንኛውም ድርድር ሕገወጥ ነው።… ፪. ከኦሮሞ ጣምራ ጦር (የኦሮሞ ልዩ ሀይል፣ ኦነግ ሸኔ፣ ጋቼና ሲርና እና ቄሮ ) ጥቃት እራሳቸውን ለመከላከል የሚሞክሮ ንጽሀን ዐማሮችን አብይ አህመድ “የአማራ ሼኔ” ሲሉ ተሰምተዋል። ይህ አባባል ዐማራን በቀጣይነት ለመጭፍጭፍ ብሎም ዘር ለማጥፋት የጠነሰሱትን ሴራ አመላካች ነው። በወለጋ ዐማራዎች ላይ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት ባስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን። ፫. ለወገኖቻችን ድምጽ የሆኑት ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋጆች፣ የተማሪዎች ማኅበር አምራሮች፣ ፋኖዎች እንዲሁም ሌሎች የሕሊና እስረኞች ሁሉም ዐማራ አካባቢ ሳይገድበው ድምፅ ሆኖ እንዲያስፈታቸው የትግል ጥሪ እናቀርባለን። ፬. አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ርዕሰ ከተማ ሆና ሳለ መጀመሪያም በለማ መገርሳ ነባሩን የሕዝብ አሰፋፈር ለመቀየር የሄደበት የማህበራዊ ምንድስና አካሄድ አሁንም የአብይ አደገኛ አመራር የአዲስ አበባን ሕዝብ ሰላማዊ ኑሮ እጅግ በጣም እያወከ ነው። ይህ ሴራ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ መቆም ያለበት ሲሆን የአዲስ አበባ ነዋሪም የራሱን እና የልጆቹን መብት በትግሉ እንዲያስከብር እንጠይቃለን። የታፈኑ ልጆች፣ አስተማሪዎች፣ ወላጆች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ በየትምህርት ቤቶች የሚካሂደው ወከባ እና ማንገለታት አሁኑን እንዲቆም፣ የአብይ አህመድ አስተዳድር በደም የተነከረ እጁን ከአዲስ አበባ ሕዝብ ላይ ባስቸኳይ እንዲያነሳ እንጠይቃለን። ፭. የአብይ አህመድ ኦሮሙማ፣ የትህነግ እና የብአዴን መሪዎች እንዲሁም በዘር ማጣፋት (Genocide) የተሳተፉትን ሁሉ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ በሚደረገው ትግል መላው ዐማራ እና አገር ወዳድ ኢትየጵያውያን በንቃት እንዲሳትፉ እንጠይቃለን። ፮. ትህነግ በዐማራው እልክ አስጨራሽ ትግል ከአራት ኪሎ የወጣች ብትሆንም ብዙ መሰዋዕትነት የተከፈለበት የሥርዓት ለውጥ ትግል በአብይ አህመድ ወዲያው የተጠለፈ በመሆኑና ኢትዮጵያ ይበልጥ “ከድጡ ወደ ማጡ” እየገባች በመሆኑ የአብይ አህመድ መንግሥት በቃህ ሊባል ስለሚገባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለጋራ አገር ሲል የየራሱን የትግል አስተዋዕፆ ማድረግ ይዋል ይደር የማይባል በመሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የትግል ጥሪ እናቀርባለን። ፯. በመጨረሻም ሁሉም ዐማራ የመደራጀትን አስፈላጊነት አምኖ በመቀበል፣ ዛሬ ነገ ሳይል፣ ምንም ቦታ ሳያግደው በተጠናከረ ሁኔታ እንዲደራጅና የትውልድ አደራውን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ዓለም አቀፍ የዐማራ ማኅበራት ፈራሚ ማህበራት:- 1. በሰሜን አሜሪካ የአማራ ማህበራት ፌዴሬሽን (ፋና) 2. የአማራ ማህበር በካሊፎርኒያ (ሳንዲያጎ) 3. የጆርጂያ የአማራ ማህበር 4. የአማራ ማህበር በኔቫዳ 5. የአማራ ህዝብ ሲቪክ ድርጅት ዳላስ ቴክሳስ 6. የዋሽንግተን እና አካባቢው የአማራ ማህበር 7. የአማራ ማህበር በአሜሪካ 8. የአማራ ማህበር በኮሎራዶ 9. የሎስ አንጀለስ የአማራ ማህበር 10. የአማራ ማህበር በሲያትል 11. የሜኒሶታ የአማራ ቅርስ ማህበር 12. የአማራ ባለሙያዎች ህብረት 13. የአማራ ማህበር በችካጎ 14. የአማራ ማህበር በሚችገን 15. የካናዳ የአማራ ማህበረሰብ ህብረት (ካሳ) 16. ኤድመንተን የአማራ ማህበር 17. ካልጋሪ የአማራ ማህበር 18. ደጀን ለአማራ ህልውና 19. የለንደን ኦንታሪዮ የአማራ ማህበር መድረክ 20. የብሪትሽ ኮሎምቢያ የአማራ ማህበር 21. የአማራ ጀግኖች አደራ ( ዩኬ ) 22. የመተከል ድጋፍ ድርጅት በዪኬ 23. በአማራ ህብረት ሙኒክ (ጀርመን) 24. የአማራ ማህበር በጀርመን 25. የአማራ ማህበር በፈርንሳይ 26. የአማራ ማህበር በስዊዘርላንድ 27. የአማራ አንድነት ማህበር በእስራኤል 28. የዐማራ ማህበራት ፌዴሬሽን በአውስትራሊያ 29. የዐማራ ማህበር በኩዊንስላንድ 30. የዐማራ ማህበር በኒው ሳውዝ ዌልስ አውስትራሊያ 31. ዐማራ ህብረት ሜልበርን 32. የዐማራ ማህበር በዌስተርን አውስትራሊያ 33. የአማራ እና የአማራ ቤተሰቦች ኢትዮጵያዊያን ማህበር በአክላንድ 34. የአማራ ማህበር በኒው ኢንግላንድ 35. የዌሊንግተን ኢንኮርፖሬትድ የአማራ ቤተሰቦች ማህበር 36. የአማራ ድጋፍ ተራድዖና መልሶ ማቋቋም ማህበር ክራይስትቸርች 37. የአማራ ወጣቶች ማህበር 38. የአማራ ተማሪዎች ማህበር 39. የዘር ማጥፋት መከላከል በኢትዮጵያ 40. የአማራ ሰብአዊ መብት እና የዘር ማጥፋት ማስጠንቀቂያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply