በመላው ዓለም የሚጣልና የሚባክነው የምግብ መጠን ከፍ ማለቱን የተመድ ጥናት አመለከተ።ጥናቱ እንደሚለው በአውሮፓዊኑ 2022 ዓ,ም 1,05 ቢሊየን ሜትሪክ ቶን የሚሆን ምግብ ነው የባከነው። ት…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/cUmf7_0NeFYcKZxyDWV2x0euBc5vK5S9VYtn4ZXB7ui1bAZ17WD7bNMSG53L7GdcQyGTBPKvX4fxh3pyeVKptPs_73pl_btq1R_UYHjBQvrDJY-bWNWnWZrGvjEqxr64iYZA2RXidvozlEf9XW_LwaExdouOX5GWq5RP96rz4nkE-IVW5A53zo5gZqe-k3_rMHf9YEj9fHanJB2Ulq3Vm5PQSvBcPpyTS0jPKxF-G938oPF9fLnE3eiSQdWINrQgwMKMiucwTx1lBtccgX7Da1LJnP0C4rRjoPv8a0fuMoz1JaAt2BOKL7v_RpPdcb91y3pwpjGOFNJIDkPfU0y0Dg.jpg

በመላው ዓለም የሚጣልና የሚባክነው የምግብ መጠን ከፍ ማለቱን የተመድ ጥናት አመለከተ።

ጥናቱ እንደሚለው በአውሮፓዊኑ 2022 ዓ,ም 1,05 ቢሊየን ሜትሪክ ቶን የሚሆን ምግብ ነው የባከነው።

ትላንት ይፋ የሆነው የተመድ የአካባቢ ጥበቃ መርሀግብር የባከነ ምግብ ዝርዝር ዘገባ በተጠቀሰው ዓመት የታየው የምግብ ብክነት ከዚያ አንድ ዓመት በፊት ከነበረው መጨመሩን አሳይቷል።

ጥናቱ እንደሚለውም ምግብ በሚጣልባቸው ሃገራት በአማካኝ አንድ ሰው በዓመት እስከ 79 ኪሎ ግራም ምግብ ያባክናል።

አብዛኛው በቆሻሻ መጣያ የሚወድቅ ምግብ የሚወጣው ከየመኖሪያ ቤቱ ሲሆን ይህም 60 በመቶውን ይሸፍናል።

28 በመቶውን ምግብ የሚደፉት የምግብ አቅርቦት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እና ምግቤቶች ሲሆኑ 12 በመቶው ደግሞ ከቸርቻሪዎች መሆኑንም ጥናቱ አሳይቷል።

ይህ ዘገባ ይፋ የሆነው በመላው ዓለም 783 ሚሊየን የሚሆን ሕዝብ ለከፋ ረሀብ መጋለጡ በሚነገርበት በዚህ ወቅት ነው።

መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply