በመላው ዳውሮ ዞን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መከሰቱ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት 1:30 ላይ ቤቶችን ሳይቀር ያንቀጣቀጠ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ማጋ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/hE_Z6Syly97Vni6uCbZZu_92oOpOJQF0ci-w-0cagUAl0CRlhYvfo3hGRh5MAit-lV9ak-KOvh80tfXkK0zjxkSIY_4oU8COsrVznpUfpujOKKsH05t9LG_nRwSr6xOdbII095oYRQHwI35-p_RF_9psXlJkOk5aHqS9WmfRfoRd_Fdo1hlJZLNWFNvrya8R4MisOMWvjPINmbQThwhzuvk9S7hOx85qnu5t6SpJ13XFc-JC9D_Jl3bxl5icfmRJXmX_g-NnRbeZ9WEbua9_0pS_Z0_5eZguasPC2QEFeKELJNoiiBkJNQWAlVjuy2Gjcp9H6w_ZoI58Tx3CW5IDtg.jpg

በመላው ዳውሮ ዞን የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ መከሰቱ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳውሮ ዞን ዛሬ ጠዋት 1:30 ላይ ቤቶችን ሳይቀር ያንቀጣቀጠ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ማጋጠሙ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

የተቺ ወረዳ ፖሊስ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ብርሀኑ ጠንክር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የመሬት መንቀጥቀጡ መላው ዳውሮን ያዳረሰ ነው ብለዋል።

በዞኑ ከዚህ በፊት በዚህ ልክ የሚሆን የመሬት መንቀጥቀጥ ደርሶ እንደማያውቅ ምክትል ኢንስፔክተር ተናግረዋል።

ጠዋት በዞኑ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ቤቶች ጭምር የነቀነቀ እንደነበረም ገልጸዋል።

የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ ታርጫ ጨምሮ በሁሉም የዞኑ ወረዳዎች አደጋው መድረሱን ነው የተገለጸው።

በተፈጠረው የመሬት መንሸጥቀጥ እስካሁን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት አልታወቀም ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም በዞኑ ከደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር በተያያዘ የሚወጡ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያቀርብ ይሆናል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply