በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የደም እጥረት ማጋጠሙ ተነገረ፡፡

የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት በቀን የሚሰበሰበው የደም መጠን በእጥፍ ቀንሷል ሲል አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደንበኞች አስተባባሪ ዶ/ር ተመስገን አበጀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በአሁኑ ሰአት በክልሎች እና በመላ ሀገሪቱ የደም ፈላጊዎች መጠን ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህ የተነሳም የኦ እና የፕሌትሌት የደም አይነቶች እጥረት መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ በቀን ከ400 ቀረጢት በላይ ይሰበሰብ የነበረ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ግን 200 ቀረጢት ደም ብቻ እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተለይም በማእከል የደም ልገሳም እጅጉን መቀዛቀዙን ዶ/ር ተመስገን ተናግረዋል፡፡

የደም መለገስ ባህሉ የተቀዛቀዘበት ዋነኛ ምክንያት ወቅቱ የጾም ወቅት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ መሆኑም ተገልጻል፡፡

በአማካይ በወር እስከ 34ሺህ ቀረጢት ደም እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን አሁን በእጥፍ መቀነሱን ይህም አሁን ባለው ሁኔታ የቀን ፍላጎት ሟሟላት አልተቻለም ሲሉ ዶ/ር ተመስገን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 30 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply