በመላ ሃገሪቱ የጥምቀት በዓል ያለጸጥታ ችግር መከበሩን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ጥር 10 እና ጥር 11 ቀን 2016 ዓ.ም የተከበረው የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በመላ ሃገሪቱ በሰላም ተጠናቋል ሲ…

በመላ ሃገሪቱ የጥምቀት በዓል ያለጸጥታ ችግር መከበሩን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ጥር 10 እና ጥር 11 ቀን 2016 ዓ.ም የተከበረው የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በመላ ሃገሪቱ በሰላም ተጠናቋል ሲል ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገራችን ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በሰላማዊ ሁኔታ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል ብሏል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሚዲያ እና የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ ለጣበያችን እንደተናገሩት የሃይማኖት አባቶች፣ የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች እና የበዓሉ ታዳሚዎች በየደረጃው ከሚገኙት የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በመሥራታቸው በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሯል ብለዋል፡፡

በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት በማስቀደም ከዋዜማ ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥበቃና እጀባ ተግባራትን በማከናወን በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር መከበሩን ተናግረዋል፡፡

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ አክሎም የሃይማኖት አባቶች፣ የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች፣ ምዕመናን እና የበዓሉ ታዳሚዎች በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ሲሰሩ እንደነበረም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያቶች በምታከብራቸው ሃይማኖታዊም ሆነ ህዝባዊ በዓላት ልክ እንደዚህ በትብብር ከተሰራ ሁሌም ሰላማዊ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply