በመራዊ ከተማ “የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም” አለ መንግስት

የኢትዮጵያ መንግሥት በመራዊ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን የ45 ሰላማዊ ሰዎች ግድያ አስተባበለ።

በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ “የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በመራዊ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን የ45 ሰላማዊ ሰዎች ግድያ አስተባበለ። በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ “የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም” ሲሉ ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጥር 20 ቀን 2016 በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ከተደረገ በኋላ “በሲቪል ሰዎች ላይ ስለደረሰው ጉዳት” ምርመራ እያካሔደ መሆኑን ትላንት ማክሰኞ አስታውቋል።
መንግሥታዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመራዊ ከተማ “ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎችን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ‘ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል’ በሚል ምክንያት ከሕግ ውጭ መግደላቸውን” እንዳረጋገጠ ይፋ አድርጓል። 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን  የካቲት 5 ቀን 2016 ባወጣው መግለጫ “‘የፋኖ አባላት ናቸው’ በሚል ተጠርጥረው የተያዙ እና ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሰዎች በተመሳሳይ ሁኔታ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል” ብሏል። 

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር አረጋግጠዋል።

ታጣቂዎቹ “በተለያዩ አቅጣጫዎች መከላከያ ሠራዊቱ የሰፈረበትን ካምፕ በአራት አቅጣጫ በማፈን መሣሪያ እና ሎጂስቲኩን ለመዝረፍ በመንቀሳቀሳቸው ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ ነው እርምጃ የወሰደው” ሲሉ ተናግረዋል።  

የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply