በመርጦ ለማርያም እና በጎንቻ መካከል ባለ አካባቢ ፋኖዎችን እንስማማ በሚል ሽማግሌ እየላኩ ያሉ አካላት በክህደት በጎን ልጆችን ለማስመታት እንቅስቃሴ እያደረጉ ስለመሆኑ ተገልጧል። የአማራ ሚ…

በመርጦ ለማርያም እና በጎንቻ መካከል ባለ አካባቢ ፋኖዎችን እንስማማ በሚል ሽማግሌ እየላኩ ያሉ አካላት በክህደት በጎን ልጆችን ለማስመታት እንቅስቃሴ እያደረጉ ስለመሆኑ ተገልጧል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 4/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በምስራቅ ጎጃም ዞን በመርጦ ለማርያም እና በጎንቻ መካከል ባለ አንድ አካባቢ ፋኖዎችን እንስማማ በሚል ሽማግሌ እየላኩ ያሉ አካላት በክህደት በጥምር ኃይል ልጆችን ለማስመታት እንቅስቃሴ እያደረጉ ስለመሆኑ ለአሚማ የገለጹት የአካባቢው ምንጮች ይህ ራስን በራስ የማጥቃት አካሄድ ሊቆም ይገባል ብለዋል። የአካባቢው ፖሊስ እና ሚሊሻ በዞን፣ በጎንቻና በመርጦ ለማሪያም ወረዳዎች ጥምር ኃይል በጎንቻ እና በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ያሉ ፋኖዎች ላይ ጉዳት ባይደርስም “ይጠፈት” ከሚባል አካባቢ ግንቦት 1/2015 ማምሻውን ተኩስ ከፍተውባቸው እንደነበር ተገልጧል። አሁንም በጎን እንስማማ በሚል ሽማግሌ እየላኩ ተኩስ ሊከፍቱባቸው ዝግጅት ስለመጨረሳቸው የተናገሩት ምንጮች የአካባቢው ማህበረሰብ ከፋኖ ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል። በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ሸፍጥ በተሞላበት መልኩ ሽምግልና በማለት በህዝብ ልጆች ላይ ተኩስ በመክፈት ታሪክ እንዳያጠፋ ጥሪ ቀርቧል። በተለይም በመርጦ ለማርያም እና በጎንቻ ሲሶ እነብሴ ሳር ምድር በ031 ቀበሌ ልዩ ስሙ አባ ሚኖስ እና ይጠፈት በተባሉ አካባቢዎች ጥንቃቄ እንዲደረግ ተጠይቋል። አባሚኖስ እና ደንበዛ በሚባሉ አካባቢዎች በኩል አድርጎ ወደ ይጠፈት በርካታ የልዩ ኃይል ልብስ የለበሰ ኃይል ግንቦት 2/2015 ከሰዓት ጀምሮ ሲገባ ተመልክተናል፤ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply