በመቀሌ እና በማይጨው ጥመቅት በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡ከአስከፊ ጦርነት ማግስት በማገገም ላይ በምትገኘው መቀሌ ከተማ የጥምቀት በዓል ለማክበር ዝግጅት…

በመቀሌ እና በማይጨው ጥመቅት በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ከአስከፊ ጦርነት ማግስት በማገገም ላይ በምትገኘው መቀሌ ከተማ የጥምቀት በዓል ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የመቀሌ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

አሁን ያለው ሁኔታ በመረጋጋቱ   በዓላትን  ያለምንም የፀጥታ ችግር   በነፃነት ለማክበር  ዝግጅት መጠናቀቁን    የመቀሌ ከተማ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የመስህብ ቱሪዝም ባለሙያ አቶ ፍስሃ ዘርዓብሩክ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን    አሁን ክልሉ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግርና ድርቁ የቀጠለበት   ሁኔታ  ቢሆንም የከተራ እና   የጥምቀት በአልን  በተሻለ መንገድ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በትግራይ  ክልል   በመቀሌ በአዲግራት እንዲሁም በማይጨው    የጥምቀት በዓል  በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ሰምተናል፡፡

በተጨማሪም   በሁሉም  የክልሉ    የከተማም ሆነ የገጠር አካባቢዎች እንደዚህ ቀደሙ በዓሉን ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በዓሉንም በሰላም ተከብሮ ለማጠናቀቅ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም አቶ ፍስሃ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

አቤል ደጀኔ

ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply